#Update " በአንዋር መስጂድ የነበሩ በቁጥር እጅግ በርካታ ሰዎች በሰላም እንዲወጡ ተደርጓል " - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ እና የበላይ አመራሮች በአንዋር መስጂድ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የማረጋጋት ስራ በመስራት አንድ ሸሂድ (መስዋእት) የሆነ ሙስሊም እና ጉዳት የደረሰባቸውን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ማድረጋቸውን ም/ቤቱ አሳውቋል። የጁመዓ ሰላት ለመስገድ በአንዋር መስጂድ የተገኙና በተፈጠረው ችግር ምክንያት በመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ታግተው የቆዩ ምእመናንም ወደየቤታቸው #በሰላም ሸኝተዋል። አንድም ሰው እንዳልቀረ ካረጋገጡ በኃላ አመራሮቹ የመስጂዱን ቅጥር ጊቢ ለቀው መውጣታቸው ተገልጿል። ከፍተኛ ም/ቤቱ ፤ " ለሞቱት ጀነት እንዲወፍቃቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ለተጎዱትም ቶሎ ማገገምን ይቸር ዘንድ አላህን እንጠይቃለን " ብሏል። በቀጣይ ህዝበ ሙስሊሙ እየተፈፀሙበት ያለውን አላግባብ የመብት ጥሰቶች በተገቢው መልኩ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ጉበኤ ውሳኔ መሰረት የተቋቋመውን ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴን እና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የሚሰጠውን አቅጣጫ እንደ መሪ ተቋም በማክበር ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል። መረጃው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ነው። https://t.me/wektawi1mereja 2.4K views17:54