Get Mystery Box with random crypto!

በዕለተ አርብ አጫጭር መረጃዎች በታላቁ አንዋር መስጂድና አካባቢው በሙስሊም ምዕመናን እና በ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

በዕለተ አርብ አጫጭር መረጃዎች

በታላቁ አንዋር መስጂድና አካባቢው በሙስሊም ምዕመናን እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ  አለመግባባት የሰው ነፍስ መጥፋቱ ተሰምቷል። ባለፈው ሳምንት እንዳጋጠመው ሁሉ ዛሬም ዐርብ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም. ከተካሄደው የጁመዓ ሶላት በኋላ በአንዋር መስጂድ አካባቢው የተኩስ ድምጽ መሰማቱን እና የሞቱ እና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸው ተነግሯል። ተመሳሳይ ተቃውሞ ከአዲስ አበባ ውጪ በአንዳንድ አካባቢዎች መከሰቱ የተሰማ ሲሆን፣ ከእስልምና ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ወይም ከፖሊስ ስለተከሰተው ችግር እና ስለደረሰ ጉዳት አስካሁን የተባለ ነገር የለም።

አቶ ዘመነ ካሴ በመስከረም ወር በቁጥጥር ሥር ውሎ  በባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ የ7 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቶት እንደነበር ይታወሳል። በከባድ የሰው መግደል ወንጀል  ተከሶ የነበረው፤ የአቶ ዘመነ ካሴ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ ዐቃቤ ሕግ መልስ ለመስጠት የክስ ችሎት ለማሰማት ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱ ተዘግቦ ቆይቷል። በመጨረሻም ዛሬ ግንቦት 25 /2015 ቀን በዋለው ችሎት፤ አቶ  ዘመነ ካሴ ከወንጀል ነፃ ነህ መባሉ ተሰምቷል።

  በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚመራ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ልዑካን ለጉብኝት ወደ ትግራይ ክልል ለጉብኝት ወደ ሸራሮ ከተማ ያመራ ሲሆን፤ በኤርትራ ወታደሮች ክልከላ እንደገጠመው ተገልጿል። ቡድኑ ወደ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ለጉብኝት ተንቀሳቅሶ እንደነበረ እና የእርዳታ ተደራሽነት ለመታዘብ እንደሞከረ ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ  ኤርትራዊያን ስደተኞች ለእስር መዳረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል። ኢሰመኮ በመግለጫው ስደተኞቹ “የማስረጃ ሰነድ የላችሁም” በሚል ምክንያት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ጠቁሟል። እንዲሁም ክስ ሳይመሠረትባቸው በእስር የቆዩ መኖራቸውን እና በተለያየ ጊዜ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ከእስር የተለቀቁ መኖራቸውንም ኮሚሽኑ አመላክቷል።

የዩክሬን ባለሥልጣናት በዋና ከተማዋ  ኪየቭ ላይ የተነጣጠሩ፣ ከ30 በላይ የሩስያ ሚሳኤሎችንና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል። የዩክሬን አየር ኃይል፣ ዛሬ ዐርብ በሰጠው መግለጫ፣ በሩስያ የተተኮሱ 15 ክሩዝ ሚሳኤሎች እና ለጥቃት የተሠማሩ 21 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ በአየር መከላከያ ሥርዐታቸው ተመትተው መክሸፋቸውንና መውደቃቸውን አስታውቋል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja