Get Mystery Box with random crypto!

አጫጭር መረጃዎች በሩሲያ ዉስጥ የተፈጠረዉ ዉጊያ በተመለከተ የዋግነር አለቃ ፕሪጎዝሂን ወደ ሞስ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

አጫጭር መረጃዎች በሩሲያ ዉስጥ የተፈጠረዉ ዉጊያ በተመለከተ

የዋግነር አለቃ ፕሪጎዝሂን ወደ ሞስኮ እየገሰገሱ የነበሩትን ተዋጊዎቻቸው ደም መፋሰስን ለማስወገድ ወደ ኃላ በመመለስ ወደ ጦር ሰፈራቸው እንዲገተቡ ማዘዛቸዉ ተሰምቷል፡፡ፕሪጎዝሂን እንዳሉት ተዋጊዎቹ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ 200 ኪ.ሜ ወደ ሞስኮ ተጉዘዋል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ  የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን "በጣም ፈርተዋል" ቅጥረኛ ወታደሮ ወደ ሞስኮ ሲገፉ የሆነ ቦታ ተደብቀዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምዕራባውያን ሀገራት የዋግነር ቅጥረኛ ቡድንን "የሩሶፎቢክ(የሩሲያ ጥላቻ) ግባቸውን ለማሳካት" እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቋል።

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ፅህፈት ቤት ሁኔታውን ለማስታገስ ከዋግነር መሪ ፕሪጎዝሂን ጋር ስምምነት እንደፈፀሙ ተናግረዋል ።በቤላሩስ ፕሬዝዳንት ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ላይ በተሰራጨው መረጃ ፕሪጎዝሂን በመላው ሩሲያ የሚያደርጉትን የዋግነር ተዋጊዎች እንቅስቃሴ ለማስቆም ተስማምተዋል፡፡

እስራኤል ዜጎቿ በሩሲያ የሚኖራቸውን ቆይታ ወይም የጉዞ እቅዳቸውን እንደገና እንዲያጤኑበት አሳስባለች።ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የጸጥታ ሃላፊዎችን በነገው እለት ለማነጋገር ቀጠሮ መያዙን የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣዉ  መግለጫ አስታውቋል።

የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌይ ሶቢያኒን የዋግነር ቅጥረኛ ቡድን ኃይሎች የሩሲያን ወታደራዊ አመራር ለማስወገድ ወደ ከተማዋ ሲንቀሳቀሱ በዋና ከተማው ውስጥ ያለው ሁኔታ "አስቸጋሪ" እንደሆነ አስጠንቅቀዋል፡፡“ሁኔታው አስቸጋሪ ነው። በተቻለ መጠን በከተማው ዙሪያ ከመጓዝ እንድትቆጠብ እጠይቃለሁ ፣ የመንገድ መዘጋት ሊኖር እንደሚችል በማስጠንቀቅ ሰኞ ስራ እንደማይኖር“ አስታውቀዋል ።

ኢራን በሩሲያ ፌደሬሽን የህግ የበላይነትን እንደምትደግፍ በመግለጽ የተፈጠረወቁን ችግር እንደ ውስጣዊ የሩሲያ ጉዳይ ትቆጥራለች ሲሉ የኢራን መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ገልፀዋል ።

ፈረንሣይ በሩሲያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ "ከፍተኛ ተለዋዋጭነት" ያለዉ በመሆኑነ ወደ ሩሲያ ዜጎቿ ከሚደርጉት  ጉዞ እንዲቆጠቡ መክራለች፡፡

ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ቱርክ በሩሲያ ውስጥ ለተፈጠረዉ አመጽ “ሰላማዊ መፍትሄ” ለመፈለግ ዝግጁ መሆኗን ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ባደረጉት ንግግር መግለጻቸዉን የቱርክ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የሩስያ የቅርብ አጋር የሆነችው ቤላሩስ በዋግነር ቅጥረኛ ቡድን እየተካሄደ ያለው የትጥቅ አመጽ ለምዕራባውያን ሀገራት "ስጦታ" እንደሆነ በመግለጽ አመፁ "አደጋ" ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja