Get Mystery Box with random crypto!

Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

የሰርጥ አድራሻ: @wasulife
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 200.89K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ደህና መጡ‼
✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed
✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife
ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-20 18:45:49 የአማራ ክልል ነጋዴዎች ንግድ ፍቃዳቸውን ያለቅጣት እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ማደስ ይችላሉ ተብሏል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት የንግድ ፍቃዳቸውን ማድስ አልቻሉም ለተባሉ በአማራ ክልል ለሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ ፍቃዳቸውን በድጋሚ ማደስ እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ገልጿል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በአማራ ክልል ያሉ ነጋዴዎች የንግድ ፍቃድ ማደሻ ጊዜን ለተጨማሪ ሶስት ወራት እንዲራዘም ማድረጉን አስታዉቋል።

በክልሉ ያሉ ነጋዴዎች የኦላይን የንግድና ምዝገባ ፍቃድ አገልግሎት ያለ ቅጣት ማደሻ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ እንዲራዘም የተደረገዉ በጥር ወር ላይ ቢሆንም አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በፀጥታ ችግር ምክንያት የንግድ ፍቃዳቸውን ማደስ ላልቻሉ ነጋዴዎች እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ማደስ ይችላሉ ነው ያለው።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
13.2K viewsWasu Mohammed, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 18:16:39
አዲስ አበባ ነገ የሚዘጉ መንገዶችን በተመለከተ

ነገ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ:—
• ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
• ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል
• ⁠ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ
• ⁠ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ
• ⁠ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ
• ⁠ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ
• ⁠ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ⁠ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት
• ⁠ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
• ⁠ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
• ⁠ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት
• ⁠ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት
• ⁠ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ
• ⁠ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ
• ⁠ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት
• ⁠ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ⁠ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ⁠ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት
• ⁠ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር
• ⁠ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት
• ⁠ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
• ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
• ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ እወቁልኝ ብሏል።
አዳዲስ መረጃዎችን Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
13.7K viewsWasu Mohammed, 15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 13:27:03
መልካም ዜና ነው

የአፋርና የሶማሊ ክልሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ አደራዳሪነት ሲካሄድ በቆየው የአፋርና የሶማሊ ክልሎች የእርቀ ሰላም ውይይት ሁለቱ ክልሎች ተኩስ ለማቆም ከስምምነት ደረሱ።

ይህ የተነገረው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተነሳሽነት በአል-ነሀሪ ሆቴል በአፋር እና በኢሳ በኩል ያሉ ታላላቅ ኡጋዞች እና መሪዎች የተሳተፉበት የአንድ ቀን ከግማሽ ሰፊ ውይይት ዛሬ በተጠናቀቀበት ጊዜ ነው።

የሶማሊና የአፋር ክልል ወንድማማች ሕዝቦች በመካከላቸው በተፈጠረው ያለመግባባት ሳቢያ የነበረውን አላስፈላጊ ደም መፋሰስ ለማቆምና ችግሩን በንግግር ለመፍታት እንደ መጀመሪያ እርምጃ፣ ሁለቱም ወገኖች ቃታ ከመሳብ ለመታቀብ ተስማምተዋል።

የሶማሊ ክልል ተደራዳሪ ኡጋዝ ሙስጦፋ ሙሐመድ እና የአፋር አቻቸው ሐጂ አበቶ ሙካ ሙሐመድ በሃይማኖት ተቋማችን አማካይነት ይህን መሰል እርቀ ሰላም መጀመሩ የሚያበረታታ መሆኑን ጠቅሰው፣ ችግሩ ረጅም  ዕድሜ ያለው ቢሆንም፣ የተጀመረው የሰላም ሂደት ትልቅ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም በዚሁ ጊዜ፣ ይህን የሰላም ጥረት ስኬት መነሻ በማድረግ፣ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚካሄዱ ግጭቶችን በንግግርና በድርድር የመፍታት ጥረት እንዲጀመር የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በመካሄድ ላይ ያሉ የወገን ለወገን የእርስ በርስ ግጭቶች እና አላስፈላጊ ደም መፋሰሶችን ለማቆም የንግግር፣ የውይይት እና የድርድር በሮች ሊከፈቱ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ    
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
15.3K viewsWasu Mohammed, edited  10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 13:03:25
የብልጽግና ፓርቲ “እስካሁን ለፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ ኢዜማ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር ህቡዕ “የሚዲያ ሠራዊት” አቋቁሟል መባሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቆ ፍትህ አንዲያሰፍን ጠይቋል።

ገዢው ብልፅግና ፓርቲ “የሚዲያ ሠራዊት” የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት የመንግስትን ገጽታን በሰው ሰራሽ መንገድ መገንባት እና መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ ደግሞ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ የሚሆኑ ጽሑፎችና ምስሎች ማሰራጨቱን ትላንት ቢቢሲ በምርመራ አረጋግጫለሁ ማለቱ ይታወሳል።

የፌስቡክ እናት ኩባንያ 'ሜታ' ጉዳዩን እንዳረጋገጠ ያስታወሰው ኢዜማ እንደገለጸው፤ ድርጊቱ የገዢውን ፓርቲ ሃሳብን የመግለጽ መብትን በመጨፍለቅ “አምባገነንነቱን” ከማሳየት ባለፈ “በውዳሴ ከንቱ ራስን አሸዋ ላይ የማቆም” አካሄድ ነው ሲል አሳስቧል።

የገዢው ፓርቲ ኃላፊዎች “የኃላፊነት ቦታቸውን ሊያስጠብቅላቸው የሚችል የትኛውንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለሱ” በአገር አቀፉ ምርጫ ወቅት ያደረጓቸውን ነገሮች ማስታወስ በቂ ነው ሲል ኢዜማ ገልጿል።

ድርጊቱ ከአንድ መንግስት የሚጠበቅ አይደለም ያለው ፓርቲው የሕግ አካላት በተቀመጡ የወንጀል ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠይቋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
14.7K viewsWasu Mohammed, edited  10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 13:01:34
ADVERTISMENT

ለሳምንቱ ማገባደጃ ምን አቅደዋል?
ለግብይትዎ የባንካችንን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ይጠቀሙ፡፡

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ፡-
•  ገንዘብ ለማስተላለፍ
•  የአየር ሰዓት ለመሙላት
•  ዕለታዊ የውጪ ምንዛሬ ተመን ለመመልከት
•  የሂሳብ እንቅስቃሴን ለማየት
•  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ክፍያዎችን ለመፈጸም ያስችልዎታል፡፡

በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ኑሮዎን ለማቅለል፣ ጊዜን ለመቆጠብ ፈጣንና አስተማማኝ በሆነው የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ይጠቀሙ

አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ!

     ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

      ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

የሶሻል ሚዲያ ገጾቻችንን Like, Follow እና Share ስለሚያደርጉ እናመሰግናለን!
ቲክቶክ፡https://www.tiktok.com/@nibinternationalbank
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/nib.intbank
ቴሌግራም ቻናል፡https://bit.ly/3SBzNYd
ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/nib_internationalbank/
ዩቲዩብ: htthttps://www.youtube.com/@nibinternationalbank6204ps://youtube.com/
ሊንክዲን፡ https://bit.ly/3bJUhgG
13.2K viewsWasu Mohammed, edited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 12:58:07
ወልቂጤ

“በጫካ፣ በአንዳንድ ስፍራ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ከላካችሁ ኃይል ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጣለች፤ ከሚከፍሏችሁ ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጣለች” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወልቂጤ ከተማ በተካሄደ ሰልፍ ላይ ተናገሩ።

የባህል፣ የቋንቋ እና የማንነት መገለጫዎች በተፈጥሮ የተለያዩ በመሆናቸው ይህንን መደፍጠጥ አይቻልም ያሉት ተቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ነገር ግን የኛ የቋንቋ፣ የባህል እና የአቀማመጥ ልዩነት ኢትዮጵያን የሚበትን መሆን የለበትም” ሲሉ ተደምጠዋል።

በመድረኩ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በማለት እንደገለጹት “አንድነት ኃይል ነው” የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየው የጉራጌ ሕዝብ፤ “ሊከፋፍሉን፣ ሊለዩን፣ ሊያባሉን ለሚፈልጉ፤ በየዕለቱ ገንዘባቸውንና እውቀታቸውን ለሚያጠፉ ሁሉ” ትምህርት መሆን አለበት።

“እኛ ደግሞ ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፤ የአፍሪካ የነጻነት፣ የኢኮኖሚ፣ የሰላምና የአንድነት ምሳሌ ትሆናለች እንላለን” ሲሉ ገልጸዋል።
ሃሳቦቹ በቀላሉ አይታረቁም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የጉራጌ ሕዝቦች መርካቶን ነጻ እንዳወጣችሁ፤ ዛሬ አዲስ አበባን ከሽንት፣ ከቆሻሻ፣ ከአልባብሌ እሳቤ፣ እጅግ ኋላ ቀር ከሆነ የኑሮ ዘዬ አላቀን ወደ እውነተኛ የብልጽግና ምልክት ለማሻገር የምናደርገውን ሂደት” እንድትደግፉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
13.6K viewsWasu Mohammed, edited  09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 10:41:22 ቲክቶክ እስከ አንድ ሰአት ቆይታ ያላቸው ፊልሞችን እና ቪድዮዎችን ፖሰት ማድረግ እንዲቻል መፍቀዱ ተሰምቷል።
14.5K viewsWasu Mohammed, 07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 10:32:41
በአሁኑ ወቅት ወደ ቀጥተኛ ግጭት የገቡት  እስራኤል እና ኢራን ባላንጣነታቸው የጀመረው ከአስርት አመታት በፊት ነበር

1979-የምዕራባውያን ወዳጅ እና የእስራኤል አጋር ተብለው የሚጠሩት የኢራኑ መሪ ሞሀመድ ሬዛ ሻህ አዲስ አገዛዝ በተከለው እና ጸረ-እስራኤል በሆነው እስላማዊ አብዮት ከስልጣን ተወገዱ።

1982- እስራኤል ሊባኖስን በወረረችበት ጊዜ የኢራን ሪቮሉሽናሪ ጋርድ በእዚያ ካሉ የሻይት ሙስሊሞች ጋር በመሆን ሄዝቦላን አቋቋመ።

እስራኤል ይህን ታጣቂ ቡድን በድንበሯ ላይ የሚገኝ አደገኛ ቡድን አድርጋ ማየት ጀመረች።

1983- በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላ የእስራኤል እና የምዕራባውያን ኃይሎች ከሊባኖስ እንዲወጡ አጥፎቶ ጠፊዎችን ተጠቀመ። በዚሁ አመት ህዳር ወር ቦምብ የተጠመደበት መኪና ከእስራኤል ጦር ዋና መቀመጫ ጋር እንዲጋጭ በመደረጉ ምክንያት እስራኤል ከአብዛኛው የሊባኖስ ክፍል ለቃ ወጣች።

1992-94 - አርጀንቲና እና እስራኤል፣ በአርጀንቲና ዋና ከተማ ቡነስ አይረስ በሚገኘው የእስራኤል ኢምባሲ ላይ በ1992 እና በአይሁድ ማዕከል ላይ በ1994 ጥቃት በማድረስ ኢራንን እና ሄዝቦላን ከሰሱ። ጥቃቶቹ እያንዳንዳቸው ከደርዘን በላይ ሰዎች እንዲገደሉ ምክንያት ሆነዋል።ኢራን እና ሄዝቦላ በጥቃቶቹ እጃቸው እንደሌለበት አስተባብለዋል።(አልአይን)
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
14.8K viewsWasu Mohammed, edited  07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 10:27:35
ADVERTISMENT

አዲስ ቅይጥ የንግድ ቦታ እጣ ሽያጭ

ዶ/ር አብዱ፣ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ገራዶ ጡንጂት አምባ አደባባይ ላይ የሚገኝ 3 መጋቢ መንገድ ያለው አዲስ በጨረታ የተረከብነውን የቅይጥ ንግድ ቦታ እጣ ሽያጭ ጀምረናል።

ለ10 ቀናት ብቻ በሚቆይ ልዩ ቅናሽ

ደሴ ገራዶ አዲሱ ምሪት ጡንጅት አምባ ሳይት፣,ካርታ የጨረሰ ፕላን እየተሰራለት ያለ:—

አንድ አባል ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤት እና 1 ሱቅ  በተጨማሪም አንድ የጋራ ፍሎር የሚኖረው ሲሆን እጣው በ150 ሺህ ብር እየተሸጠ ይገኛል።

የግንባታ ወጭ በአባላት የጋራ መዋጮ ይሆናል።

የሌለንን ስለማንሸጥ ከእኛ ጋር በመስራት ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ።

ለበለጠ መረጃ በማህበሩ ስልኮች:—
0937411111 ወይም 0938411111 ይደውሉ።

ታማኝነት መገለጫችን ነው።
ዶ/ር አብዱ፣ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት የማልማትና የማከፋፈል ህ/ሽ/ማ
14.4K viewsWasu Mohammed, 07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 08:44:37
ሿሿ በቲክቶክ

"ታማሚው ስለማይድን የተሰበሰበውን ብር ሰይጣን አሳስቶን አጠፋነው. . ."

ከሞተር ወድቆ ከወገብ በታች ለማይንቀሳቀሰው አለሙ ቢጫ ለተባለ ግለሰብ የተለያዩ ቲክቶከሮች የእርዳታ ገንዘብ ቢሰበስቡም ለታማሚው ብር ሳይደርስ ቀርቶ ታማሚው ባቀረበው ተማፅኖ ብሩን የሰበሰቡት ቲክቶከሮች የተወሰነ ብር ቢመልሱም ዋነኛውና በምስሉ የሚታየው ወጣት ግን 350,000 ሺህ ብር አካባቢ ለመመለስ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ሰምተናል። ለዚህም የቀረበው ምክንያት " ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ" የሚል ነበር።የቲክቶክ ሿሿ ይሏል ይሄ ነው።"ይሞታል ብለን"ያሳዝናል።
Via: ስንታየሁ ኃይሉ
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
14.6K viewsWasu Mohammed, edited  05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ