Get Mystery Box with random crypto!

መልካም ዜና ነው የአፋርና የሶማሊ ክልሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ። በኢትዮጵያ እስ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

መልካም ዜና ነው

የአፋርና የሶማሊ ክልሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ አደራዳሪነት ሲካሄድ በቆየው የአፋርና የሶማሊ ክልሎች የእርቀ ሰላም ውይይት ሁለቱ ክልሎች ተኩስ ለማቆም ከስምምነት ደረሱ።

ይህ የተነገረው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተነሳሽነት በአል-ነሀሪ ሆቴል በአፋር እና በኢሳ በኩል ያሉ ታላላቅ ኡጋዞች እና መሪዎች የተሳተፉበት የአንድ ቀን ከግማሽ ሰፊ ውይይት ዛሬ በተጠናቀቀበት ጊዜ ነው።

የሶማሊና የአፋር ክልል ወንድማማች ሕዝቦች በመካከላቸው በተፈጠረው ያለመግባባት ሳቢያ የነበረውን አላስፈላጊ ደም መፋሰስ ለማቆምና ችግሩን በንግግር ለመፍታት እንደ መጀመሪያ እርምጃ፣ ሁለቱም ወገኖች ቃታ ከመሳብ ለመታቀብ ተስማምተዋል።

የሶማሊ ክልል ተደራዳሪ ኡጋዝ ሙስጦፋ ሙሐመድ እና የአፋር አቻቸው ሐጂ አበቶ ሙካ ሙሐመድ በሃይማኖት ተቋማችን አማካይነት ይህን መሰል እርቀ ሰላም መጀመሩ የሚያበረታታ መሆኑን ጠቅሰው፣ ችግሩ ረጅም  ዕድሜ ያለው ቢሆንም፣ የተጀመረው የሰላም ሂደት ትልቅ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም በዚሁ ጊዜ፣ ይህን የሰላም ጥረት ስኬት መነሻ በማድረግ፣ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚካሄዱ ግጭቶችን በንግግርና በድርድር የመፍታት ጥረት እንዲጀመር የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በመካሄድ ላይ ያሉ የወገን ለወገን የእርስ በርስ ግጭቶች እና አላስፈላጊ ደም መፋሰሶችን ለማቆም የንግግር፣ የውይይት እና የድርድር በሮች ሊከፈቱ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ    
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g