Get Mystery Box with random crypto!

የብልጽግና ፓርቲ “እስካሁን ለፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ ኢዜ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

የብልጽግና ፓርቲ “እስካሁን ለፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ ኢዜማ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር ህቡዕ “የሚዲያ ሠራዊት” አቋቁሟል መባሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቆ ፍትህ አንዲያሰፍን ጠይቋል።

ገዢው ብልፅግና ፓርቲ “የሚዲያ ሠራዊት” የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት የመንግስትን ገጽታን በሰው ሰራሽ መንገድ መገንባት እና መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ ደግሞ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ የሚሆኑ ጽሑፎችና ምስሎች ማሰራጨቱን ትላንት ቢቢሲ በምርመራ አረጋግጫለሁ ማለቱ ይታወሳል።

የፌስቡክ እናት ኩባንያ 'ሜታ' ጉዳዩን እንዳረጋገጠ ያስታወሰው ኢዜማ እንደገለጸው፤ ድርጊቱ የገዢውን ፓርቲ ሃሳብን የመግለጽ መብትን በመጨፍለቅ “አምባገነንነቱን” ከማሳየት ባለፈ “በውዳሴ ከንቱ ራስን አሸዋ ላይ የማቆም” አካሄድ ነው ሲል አሳስቧል።

የገዢው ፓርቲ ኃላፊዎች “የኃላፊነት ቦታቸውን ሊያስጠብቅላቸው የሚችል የትኛውንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለሱ” በአገር አቀፉ ምርጫ ወቅት ያደረጓቸውን ነገሮች ማስታወስ በቂ ነው ሲል ኢዜማ ገልጿል።

ድርጊቱ ከአንድ መንግስት የሚጠበቅ አይደለም ያለው ፓርቲው የሕግ አካላት በተቀመጡ የወንጀል ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠይቋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed