Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ነገ የሚዘጉ መንገዶችን በተመለከተ ነገ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም የ2016 የ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

አዲስ አበባ ነገ የሚዘጉ መንገዶችን በተመለከተ

ነገ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ:—
• ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
• ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል
• ⁠ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ
• ⁠ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ
• ⁠ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ
• ⁠ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ
• ⁠ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ⁠ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት
• ⁠ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
• ⁠ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
• ⁠ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት
• ⁠ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት
• ⁠ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ
• ⁠ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ
• ⁠ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት
• ⁠ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ⁠ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ⁠ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት
• ⁠ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር
• ⁠ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት
• ⁠ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
• ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
• ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ እወቁልኝ ብሏል።
አዳዲስ መረጃዎችን Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed