Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል ነጋዴዎች ንግድ ፍቃዳቸውን ያለቅጣት እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ማደስ ይችላሉ ተብ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

የአማራ ክልል ነጋዴዎች ንግድ ፍቃዳቸውን ያለቅጣት እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ማደስ ይችላሉ ተብሏል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት የንግድ ፍቃዳቸውን ማድስ አልቻሉም ለተባሉ በአማራ ክልል ለሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ ፍቃዳቸውን በድጋሚ ማደስ እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ገልጿል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በአማራ ክልል ያሉ ነጋዴዎች የንግድ ፍቃድ ማደሻ ጊዜን ለተጨማሪ ሶስት ወራት እንዲራዘም ማድረጉን አስታዉቋል።

በክልሉ ያሉ ነጋዴዎች የኦላይን የንግድና ምዝገባ ፍቃድ አገልግሎት ያለ ቅጣት ማደሻ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ እንዲራዘም የተደረገዉ በጥር ወር ላይ ቢሆንም አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በፀጥታ ችግር ምክንያት የንግድ ፍቃዳቸውን ማደስ ላልቻሉ ነጋዴዎች እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ማደስ ይችላሉ ነው ያለው።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed