Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ብር ኢንጌጅ” ከግብይትና ገንዘብ መላላክ በተጨማሪ ጽሁፍ፣ ፎቶ፣ ድምጽና የቪዲ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ብር ኢንጌጅ” ከግብይትና ገንዘብ መላላክ በተጨማሪ ጽሁፍ፣ ፎቶ፣ ድምጽና የቪዲዮ ፋይሎችን መለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎት ዛሬ አስጀምሯል።

አገልግሎቱ ያለ ኢንተርኔት ክፍያ በደንበኞች መካከል መረጃዎችን መለዋወጥ ፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ክፍያዎችን መፈጸም እና መሰል አገልግሎቶችን ማግኘት ያስችላል ተብሏል፡፡

ዛሬ በይፋ አገልግሎት የጀመረው “ቴሌ ብር ኢንጌጅ” እንደ ማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃዎችን መለዋወጥ የሚያስችል ሲሆን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እና ድምጾችን መላላክ እንደሚያስችልም ተጠቁሟል፡፡

ቴሌብር በአሁኑ ወቅት:—

በሦስት ዓመት ውስጥ 44.5 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራት ችሏል።

በሦስት አመት ውስጥ 775 የገንዘብ ዝውውሮች የተደረጉ ሲሆን ከ2 ትሪሊየን ብር በላይ አንቀሳቅሷል።

ዛሬ ላይ በቀን 5 ቢሊዮን ትራንዛክሽን ይፈጸምበታል።

ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed