Get Mystery Box with random crypto!

Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

የሰርጥ አድራሻ: @wasulife
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 200.89K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ደህና መጡ‼
✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed
✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife
ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-04-13 20:12:05 ብልፅግና እና ህውሃት ዛሬ በአዲስ አበባ ተገናኝተው ምክክር ማድረግ መጀመራቸውን ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።የምክክሩ ዝርዝር ሁኔታ በግልፅ አልተብራራም።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
16.8K viewsWasu Mohammed, edited  17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 18:31:35 በጋምቤላ ክልል 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

በጋምቤላ ክልል በጆርና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት እጃቸው አለባቸው የተባሉ 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡሞድ ኡሞድ እንዳሉት በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮችና ግለሰቦች በጆር እና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር እጃቸው አለባቸው የተባሉ ናቸው ብለዋል።

በተለይም በመጋቢት 26/2016 ዓመተ ምህረት በጆር ወረዳ ለተከሰተው የሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም እጃቸው አለባቸው የተባሉ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች እና አምስት የወረዳ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በኢታንግ ልዩ ወረዳ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ለህግ እንዳይቀርቡ እንቅፋት የሆኑ ሰባት የወረዳ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ማጣራት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም በተለያዩ መድረኮች በጋምቤላ ከተማ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የሚሞክር አንድ ግለሰብ ከአመራሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውቀዋል።

በክልሉ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ ወደ ቀድሞ ሰላሙ እንዲመለስ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ኮሚሽነር ኡሞድ ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
17.7K viewsWasu Mohammed, edited  15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 18:27:12
በዲላ ከተማ አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በዲላ ከተማ አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ እስካሁን ባለው መረጃ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን በተወሰኑ ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ጉዳቱ የደረሰው ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ አካባቢ መሆኑን ያመለከተው የዲላ ከተማ ፖሊስ የተጎዱ ግለሰቦችን ወደ ሆስፒታል የመወሰድ እንዲሁም መንገድ ላይ የወደቁ ዛፎችንና የመብራት ፖሎችን ከመንገድ የማንሳት ተግባር እየተከናወነ ይገኛል ብሏል።

መረጃው የዲላ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነው።

ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
16.5K viewsWasu Mohammed, edited  15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 15:44:58
በዶዶላ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ13 ሰዎች ማለፉ ተሰማ።

አደጋው የደረሰው በኦሮሚያ ክልል ከነገሌ መስማ ከተማ ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ በአላንቱ ወረዳ ወደ ዶዶላ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ከተቃራኒ አቅጣጫ ከሚመጣ ከሲኖ ትራክ ጋር በመጋጨቱ ነው።

ጉዳት የደረሰባቸው ከ20 በላይ ሰዎች በዶዶላ እና በመዳወላቡ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ታውቋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
18.5K viewsWasu Mohammed, 12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 15:38:24
ADVERTISMENT

''በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ'' በወላይታ ሶዶ ሁምቦ እና ወላይታ መናኸሪያ ቅርንጫፍ።

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

የሶሻል ሚዲያ ገጾችን

ቲክቶክ፡https://www.tiktok.com/@nibinternationalbank
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/nib.intbank
ቴሌግራም ቻናል፡https://bit.ly/3SBzNYd
ኢንስታግራም ፡https://www.instagram.com/nib_internationalbank/
ዩቲዩብ: www.youtube.com/@nibinternationalbank6204ps://youtube.com/
ሊንክዲን፡ https://bit.ly/3bJUhgG
ዌብ ሳይት፡ www.nibbanksc.com
17.3K viewsW M, 12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 11:10:32
ነገ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ/ም የሚከበረውን 1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ
  ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
  ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው  አጎና ሲኒማ ላይ
  ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ፡፡
  ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
  ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ
  ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል  አጠገብ
  ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ  አቧሬ ሴቶች አደባባይ  ላይ
  ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
  ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ
  ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ
  ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎባ ቁጠባ አጠገብ
  ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ
  ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር  ወደ ብሔራዊ ቴአትር  ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ
ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ድረስ ሰላት እስከሚጠናቀቅ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።
12.9K viewsWasu Mohammed, 08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 08:48:55 ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አጥታለች ተብሏል

ዓለማችን በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት 9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣቷ ተገልጿል

30 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመከታተል እና ሪፖርቶችን በማውጣት የሚታወቀው ኔት ብሎክስ የ2023 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ተቋም ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከኢንተርኔት በመዝጋት ገቢ ካጡ ሀገራት መካከል ከሩሲያ በመቀጠል ከፍተኛ ገቢ ያጣች ሀገር ተብላለች፡፡

ሩሲያ 113 ሚሊዮን ዜጎቿን ከኢንተርኔት ውጪ በማድረጓ አራት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ስታጣ ኢትዮጵያ ደግሞ 30 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ተደርገዋል፡፡

ሆን ተብሎ በመንግስት እንደተወሰደ የተገለጸው ይህ ኢንተርኔት ማቋረጥ ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አሳጥቷታል ተብሏል፡፡

ሀገራት ኢንተርኔት አገልግሎቶችን የሚያቋርጡት በሶስት ምክንያት ነው የተባለ ሲሆን ተቃውሞዎችን ለማፈን፣ የሀሳብ ነጻነትን ለመገደብ እና የምርጫ ስራዎች እንዳይታወኩ በሚል እንደሆነም ተገልጿል፡፡

25 የዓለማችን ሀገራት ኢንተርኔት አቋርጠዋል የተባለ ሲሆን በኢትዮጵያ ሁሉም ማሕበራዊ የትስስር ገጾች መታገዳቸው ተገልጿል፡፡

የቀድሞ ስሙ ትዊተር ወይም ኤክስ ደግሞ ከሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል በብዙ ሀገራት ታግዷል ተብሏል፡፡

ይህ ሪፖርት አዲሱ የፈረንጆቹ 2024 ዓመትን አይመለከትም የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራ የኢንተርኔት ገደቦች አሁንም እንደተጣሉ ናቸው፡፡

በአማራ ክልል ካሳለፍነው ሀምሌ ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎት በዚሁ ጊዜ እንደተቋረጠ ይገኛል፡፡

ለስድስት ወራት በሚል የጣወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን አዋጁ ሊጠናቀቅ ቀሪ ሁለት ይቀሩታል፡፡

በአጠቃላይ በ2023 ዓመት 747 ሚሊዮን ዜጎች በመንግስታት በተወሰዱ እርምጃዎች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጣቸው ተገልጿል፡፡(Al ain)
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
14.2K viewsWasu Mohammed, 05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 08:47:58
ማስታወቂያ

  የተከበራችሁ ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት የእጣ ባለድርሻ አባላት
የደሴ ገራዶ ጡንጅት አምባ ሳይቶችን ካርታ ተጠናቆ እጃችን ገብቷል።

አሁን ላይ በፕላን በማሰራት ሂደት ላይ እንገኛለን።ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ባደረገው ስብሰባ ወርሀዊ መዋጮ ከመጋቢት ወር መጀመር እንዳለበት ተወስኗል።

ስለሆነም በተወሰነው መሰረት የማህበሩ አባላት ወርሃዊ ክፍያ 5,000 ብር ሲሆን የመጋቢትን ወርሀዊ ክፍያ እስከ ሚያዚያ 5/2016 ከታች በተጠቀሱት የማህበሩ ሂሳብ ቁጥሮች
1.ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ=1000614550523 ወይም
2.አማራ ባንክ=8800001003165 (አጭር ቁጥር 665544) ገቢ እንድታደርጉ እናሳውቃለን።ገቢ ካደረጋችሁ በኋላ ገራዶ አዲሱ መነሃሪያ በር ላይ ከሚገኘው የማህበሩ ቢሮ ደረሰኝ መውሰድ ትችላላችሁ። 

በተመሳሳይ የሀይቅ ሳይት አባላቶች ከዚህ በፊት በተግባባንበት አግባብ ወርሃዊ ቁጠባችሁን ከላይ በተጠቀሱት የሂሳብ ቁጥሮች ገቢ ማድረግ እንዳለባችሁ ለማስታወስ እንወዳለን።

ለተጨማሪ መረጃ:
0914328862
0938411111
0937411111 ይደውሉ: ወይም
ገራዶ መነሀሪያ መውጫ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት  በሚገኘው ቢሮ በአካል በመምጣት መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

  ታማኝነት መገለጫችን ነው

ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ማልማት ና ማከፋፈል ህ/ሽ/ማ ስራ አስፈፃሚዎች።
13.2K viewsWasu Mohammed, 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 08:06:08 ነገ ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 የኢድ አልፈጥር በዓል ይከበራል።ከረመዳን ወር መጨረሻ በበዓሉ ዋዜማ ዘካቱል ፊጥር / የፍስግ ምጽዋት/ ይሰጣል።ለግንዛቤ ዝርዝር ሁኔታው ከታች ተቀምጧል።

ዘካተል ፊጥር የረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ተከትሎ በወቅቱ ሙስሊም ሁኖ በህይወት ባለ ሰው በነፍስ ወከፍ ግዴታ የሚሆን የዘካ / ሰደቃ/ አይነት ነው ፡፡

★ ዘካተል ፊጥር የተደነገገበት ጥበብ ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው ።

★ የዘካተል ፊጥር መጠን ሷዕ / ቁና/ በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኞች ነው ። ወደ ኪሎ ግራም ሲቀየር እንደየ እህሉ ክብደትና ቅለት ይለያያል ። ለምሳሌ ፣
  ★ አንድ ቁና (ሳእ) ፉርኖ ዱቄት 2 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ጤፍ 2·5 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ሩዝ 2·6 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ስንዴ 2·5 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ገብስ 2·5 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ማሽላ 2·25 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) በቆሎ 2·5 ኪሎ

☞★ ግዴታ የሚሆነው
ሙስሊም በሆነ
ረመዷን ወር ሲጠናቀቅ በህይወት የነበረ
በእለቱ ለ24 ሰዓት ለራሱና ለሚያስተዳድራቸው ሰዎች ወጪ የሚያደርገው ሀብት ኑሮት ከዚያ የተረፈ ባለው ሰው ።
☞ ★ ዘካተል ፊጥር በነፍስ ወከፍ የሚደረግ ኢባዳ ስለሆነ በቤተሰብ ስር የሚኖር ሰው ለራሱ ሚያወጣበት ነገር ካለው ቤተሰቦቹን ከመጠበቅ ራሱ ማውጣት ይኖርበታል ።

ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻው እለት ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ የኢድ ሷላት ተሰግዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው፡፡ ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ነው ። ድንገት አንድ ሰው ረስቶ ወይም ሳይመቸው ቀርቶ በወቅቱ ሳያወጣ ቢቀር ባስታወሰና በተመቸው ወቅት ማውጣት አለበት ።

★ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶችን በተመለከተ አውጪዎቹ በሀገራቸው ከሚመገቡዋቸው እህሎች ውስጥ ይሆናል ለምሳሌ እንደ ተምር ፣ ዱቄት ፣ እሩዝ ፣ በቆሎ፤ ጤፍ …. ወዘተ ባሉ የምግብ እህል አይነቶች ነው።

★ ዘካተል ፊጥር ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ነው ሚሰጠው

Credit to Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.

ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
13.2K viewsWasu Mohammed, 05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 20:11:12
የዘንድሮው ግጥምጥሞሽ ይገርማል

መጋቢት 2 የሁለቱም ፆም(ረመዳን እና አብይ ፆም)ሰኞ  በአንድ ቀን ተጀመረ

ትናንት መጋቢት 27 በእስልምና እምነት ተከታዮች የረመዳን 27ኛ ለይል ስለነበር ለይለተል ቀድር የሚጠበቅበት ታላቅ የምህረት ቀን ነበር።  በዚሁ እለት ትናንት ዓርብ መጋቢት 27 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለት የተፈፀመበት ታላቅ ቀን ሲሆን ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሳበት መጋቢት 29 እሁድ ዳግም ለፍርድ የሚመጣበት ዕለተ ምጽአቱ (ደብረ ዘይት) ነገ እሁድ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ይከበራል። በእስልምና እምነት ደግሞ ረመዳን 29ኛው ለይል የሚገባበት ሌላኛው ለይለተል ቀድር የሚጠበቅበት ታላቅ ዕለት ነው።
አላህ ፍቅርን አብዝቶ ይስጠን
@wasulife @wasumohammed
=======================
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed
14.2K viewsWasu Mohammed, edited  17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ