Get Mystery Box with random crypto!

በጋምቤላ ክልል 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ። በጋምቤላ ክልል በጆርና በ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

በጋምቤላ ክልል 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

በጋምቤላ ክልል በጆርና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት እጃቸው አለባቸው የተባሉ 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡሞድ ኡሞድ እንዳሉት በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮችና ግለሰቦች በጆር እና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር እጃቸው አለባቸው የተባሉ ናቸው ብለዋል።

በተለይም በመጋቢት 26/2016 ዓመተ ምህረት በጆር ወረዳ ለተከሰተው የሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም እጃቸው አለባቸው የተባሉ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች እና አምስት የወረዳ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በኢታንግ ልዩ ወረዳ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ለህግ እንዳይቀርቡ እንቅፋት የሆኑ ሰባት የወረዳ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ማጣራት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም በተለያዩ መድረኮች በጋምቤላ ከተማ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የሚሞክር አንድ ግለሰብ ከአመራሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውቀዋል።

በክልሉ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ ወደ ቀድሞ ሰላሙ እንዲመለስ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ኮሚሽነር ኡሞድ ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed