Get Mystery Box with random crypto!

ነገ ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 የኢድ አልፈጥር በዓል ይከበራል።ከረመዳን ወር መጨረሻ በበዓሉ ዋዜማ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

ነገ ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 የኢድ አልፈጥር በዓል ይከበራል።ከረመዳን ወር መጨረሻ በበዓሉ ዋዜማ ዘካቱል ፊጥር / የፍስግ ምጽዋት/ ይሰጣል።ለግንዛቤ ዝርዝር ሁኔታው ከታች ተቀምጧል።

ዘካተል ፊጥር የረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ተከትሎ በወቅቱ ሙስሊም ሁኖ በህይወት ባለ ሰው በነፍስ ወከፍ ግዴታ የሚሆን የዘካ / ሰደቃ/ አይነት ነው ፡፡

★ ዘካተል ፊጥር የተደነገገበት ጥበብ ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው ።

★ የዘካተል ፊጥር መጠን ሷዕ / ቁና/ በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኞች ነው ። ወደ ኪሎ ግራም ሲቀየር እንደየ እህሉ ክብደትና ቅለት ይለያያል ። ለምሳሌ ፣
  ★ አንድ ቁና (ሳእ) ፉርኖ ዱቄት 2 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ጤፍ 2·5 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ሩዝ 2·6 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ስንዴ 2·5 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ገብስ 2·5 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) ማሽላ 2·25 ኪሎ
★አንድ ቁና (ሳእ) በቆሎ 2·5 ኪሎ

☞★ ግዴታ የሚሆነው
ሙስሊም በሆነ
ረመዷን ወር ሲጠናቀቅ በህይወት የነበረ
በእለቱ ለ24 ሰዓት ለራሱና ለሚያስተዳድራቸው ሰዎች ወጪ የሚያደርገው ሀብት ኑሮት ከዚያ የተረፈ ባለው ሰው ።
☞ ★ ዘካተል ፊጥር በነፍስ ወከፍ የሚደረግ ኢባዳ ስለሆነ በቤተሰብ ስር የሚኖር ሰው ለራሱ ሚያወጣበት ነገር ካለው ቤተሰቦቹን ከመጠበቅ ራሱ ማውጣት ይኖርበታል ።

ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻው እለት ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ የኢድ ሷላት ተሰግዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው፡፡ ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ነው ። ድንገት አንድ ሰው ረስቶ ወይም ሳይመቸው ቀርቶ በወቅቱ ሳያወጣ ቢቀር ባስታወሰና በተመቸው ወቅት ማውጣት አለበት ።

★ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶችን በተመለከተ አውጪዎቹ በሀገራቸው ከሚመገቡዋቸው እህሎች ውስጥ ይሆናል ለምሳሌ እንደ ተምር ፣ ዱቄት ፣ እሩዝ ፣ በቆሎ፤ ጤፍ …. ወዘተ ባሉ የምግብ እህል አይነቶች ነው።

★ ዘካተል ፊጥር ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ነው ሚሰጠው

Credit to Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.

ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed