Get Mystery Box with random crypto!

ወልቂጤ “በጫካ፣ በአንዳንድ ስፍራ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ከላካችሁ ኃይል ይልቅ ኢትዮጵያ ትበ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

ወልቂጤ

“በጫካ፣ በአንዳንድ ስፍራ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ከላካችሁ ኃይል ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጣለች፤ ከሚከፍሏችሁ ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጣለች” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወልቂጤ ከተማ በተካሄደ ሰልፍ ላይ ተናገሩ።

የባህል፣ የቋንቋ እና የማንነት መገለጫዎች በተፈጥሮ የተለያዩ በመሆናቸው ይህንን መደፍጠጥ አይቻልም ያሉት ተቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ነገር ግን የኛ የቋንቋ፣ የባህል እና የአቀማመጥ ልዩነት ኢትዮጵያን የሚበትን መሆን የለበትም” ሲሉ ተደምጠዋል።

በመድረኩ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በማለት እንደገለጹት “አንድነት ኃይል ነው” የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየው የጉራጌ ሕዝብ፤ “ሊከፋፍሉን፣ ሊለዩን፣ ሊያባሉን ለሚፈልጉ፤ በየዕለቱ ገንዘባቸውንና እውቀታቸውን ለሚያጠፉ ሁሉ” ትምህርት መሆን አለበት።

“እኛ ደግሞ ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፤ የአፍሪካ የነጻነት፣ የኢኮኖሚ፣ የሰላምና የአንድነት ምሳሌ ትሆናለች እንላለን” ሲሉ ገልጸዋል።
ሃሳቦቹ በቀላሉ አይታረቁም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የጉራጌ ሕዝቦች መርካቶን ነጻ እንዳወጣችሁ፤ ዛሬ አዲስ አበባን ከሽንት፣ ከቆሻሻ፣ ከአልባብሌ እሳቤ፣ እጅግ ኋላ ቀር ከሆነ የኑሮ ዘዬ አላቀን ወደ እውነተኛ የብልጽግና ምልክት ለማሻገር የምናደርገውን ሂደት” እንድትደግፉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed