Get Mystery Box with random crypto!

በአሁኑ ወቅት ወደ ቀጥተኛ ግጭት የገቡት  እስራኤል እና ኢራን ባላንጣነታቸው የጀመረው ከአስርት አ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

በአሁኑ ወቅት ወደ ቀጥተኛ ግጭት የገቡት  እስራኤል እና ኢራን ባላንጣነታቸው የጀመረው ከአስርት አመታት በፊት ነበር

1979-የምዕራባውያን ወዳጅ እና የእስራኤል አጋር ተብለው የሚጠሩት የኢራኑ መሪ ሞሀመድ ሬዛ ሻህ አዲስ አገዛዝ በተከለው እና ጸረ-እስራኤል በሆነው እስላማዊ አብዮት ከስልጣን ተወገዱ።

1982- እስራኤል ሊባኖስን በወረረችበት ጊዜ የኢራን ሪቮሉሽናሪ ጋርድ በእዚያ ካሉ የሻይት ሙስሊሞች ጋር በመሆን ሄዝቦላን አቋቋመ።

እስራኤል ይህን ታጣቂ ቡድን በድንበሯ ላይ የሚገኝ አደገኛ ቡድን አድርጋ ማየት ጀመረች።

1983- በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላ የእስራኤል እና የምዕራባውያን ኃይሎች ከሊባኖስ እንዲወጡ አጥፎቶ ጠፊዎችን ተጠቀመ። በዚሁ አመት ህዳር ወር ቦምብ የተጠመደበት መኪና ከእስራኤል ጦር ዋና መቀመጫ ጋር እንዲጋጭ በመደረጉ ምክንያት እስራኤል ከአብዛኛው የሊባኖስ ክፍል ለቃ ወጣች።

1992-94 - አርጀንቲና እና እስራኤል፣ በአርጀንቲና ዋና ከተማ ቡነስ አይረስ በሚገኘው የእስራኤል ኢምባሲ ላይ በ1992 እና በአይሁድ ማዕከል ላይ በ1994 ጥቃት በማድረስ ኢራንን እና ሄዝቦላን ከሰሱ። ጥቃቶቹ እያንዳንዳቸው ከደርዘን በላይ ሰዎች እንዲገደሉ ምክንያት ሆነዋል።ኢራን እና ሄዝቦላ በጥቃቶቹ እጃቸው እንደሌለበት አስተባብለዋል።(አልአይን)
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed