Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education®

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education®
የሰርጥ አድራሻ: @tmihirt_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Student_Comment_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-11-12 12:33:23 የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ውጤቱ እስከ ህዳር 15 ድረስ ይወጣል የሚሉ መረጃዎች ሲዘዋወሩ ተመልክተናል በእርግጥ የፈተና ውጤቱ የሚገለፅበት በዚህ ጊዜ ተብሎ ባይገለፅም ፈተናው በ2ዙር ተሰጥቶ የሁለቱንም ዙር ፈተና ውጤት በአንድላይ አጠቃሎ ውጤቱ ይፋ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር ገልፆ ነበር የፈተናው ዙር እርማት ተጠናቋል አሁን የሚጠበቀዉ ሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ተፈትነው ውጤቱን ይፋ ማድረግ ነው
ሆኖም ሁለተኛ ዙር ፈተና መች እንደሚሰጥ የተገለፀ ነገር ባይኖርም ተማሪዎች የመጀመሪያ ዙር ፈተና ውጤት እንዲገለፅ በተደጋጋሚ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ
በአጭሩ ውጤቱ እስከ እዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል ፈተናው ት/ት ሚኒስቴር ባቀደው መሰረት ከሄደ ደግሞ ሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ፈተናው እስኪወስዱ ድረስ መጠበቅ የማይቀር ነው
ተማሪዎችም እንደተለመደው ተረጋግተው እንዲጠብቁ ተጠይቋል

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
605 viewsedited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 13:05:57
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግል ተማሪዎች ክፍያን በእጥፍ መጨመሩ ቅሬታ አስነሳ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለግል ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ላይ የ100 በመቶ ጭማሪ ማድረጉ ከተማሪዎች ቅሬታ ቀርቦበታል።

በዚህም ከፍተኛ ቅሬታ አድሮብናል ያሉት ተማሪዎቹ፣ በተለይ በዚህ ዓመት ለመማር እቅድ ይዘው የነበሩ አዲስ ተመዝጋቢዎች፣ የመግቢያ ፈተናውን ከተፈተኑ በኋላ የዋጋ ጭማሪውን ሲመለከቱ ብዙዎች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል።

ከገንዘብ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ለተማሪዎች መብታቸውን የሚያስከብርላቸው ጠንካራ ተቋም ባለመኖሩ የትምህርት ተቋማት ብዝበዛ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.2K viewsedited  10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 07:38:31
የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃዎች ስለሚበዛ ጥንቃቄ አድርጉ።

ውጤቱ የሚመጣው ያልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኋላ አንድ ላይ የሚመጣ ይሆናል።

በሰላም እና ፀጥታ ምክንያት ፈተና ያልተቀመጡ ተማሪዎች በቅርብ ጊዜ ይፈተናሉ። (ከ 56,000 በላይ ተማሪዎች )

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
954 viewsedited  04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 12:29:46
ውጤት ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ይለቀቃል ሲሉ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
2.4K viewsedited  09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 15:12:37 #MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ?

- "የፈተና ዝግጅት እና ህትመት" ከቀድሞው እንዲለይ በኮድ ብዛት እና በገፅ አወቃቀር በመለየት በሁለቱም የትምህርት መስኮች " 12 ኮድ " እንዲኖር እና የመለያ ኮዱ ከሚታወቅበት 2 ኮድ ወደ 3 ተቀይሮ ፈተናው ተሰጥቷል።

- #ስልክ እና ማንኛውም #ኤሌክትሮኒክ_መሳሪዎችን ተፈታኞች ይዘው እንዳይመጡ መልዕክት ቢተላለፍም በ33 የፈተና ጣቢያዎች 59 ተፈታኞች #ስልክ_ይዘው ገብተው ለመጠቀም ሙከራ አድርገው ተይዘዋል።
ጫት፣
አደንዛዥ ዕፅ፣
ሲጋራ፣
ስለታማ ነገሮች፣
ጥይት፣
አልኮል ..... ወዘተ ተፈታኞች ይዘው በመምጣት በተለያየ መልክ ለማስገባትና በአንዳንድ ቦታዎችም ለመጠቀም ሙከራ አድርገዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ " ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ግቢ " የሚወስደው ድልድይ በመደርመሱ ምክንያት 451 ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል ፤ 1 ተማሪ ህይወቱ ሲያልፍ 232 ተማሪዎች ቀላል የአካል ጉዳት ፣ 201 ተማሪዎች መካከለኛ ጉዳት ፣ 13 ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ፣ 5 ተማሪዎች በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ 5 የፀጥታ ኃይሎች እና 2 ፈተና አስፈፃሚዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- " በሶስት ዩኒቨርሲቲዎች " ቀደም ሲል በነበር የጤና እክል ምክንያት 3 ተማሪዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ በጉዞ ወቅት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ የተወሰኑ ተማሪዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ፈተና መውሰድ ያልቻሉና በከፊል የተፈተኑ በአንድ ወር ጊዜ የሚዘጋጀውን ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል። ተፈታኞቹ የጤና ሁኔታቸው ለፈተናው የማያበቃቸው ካሉ ከ2015 ዓ/ም ተፈታኞች ጋር በመደበኛነት እንዳፈተኑ ይደረጋል።

- " ፈተና አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ዳግም በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እንድል አይሰጣቸውም፤ በግል በ2015 ዓ.ም የመፈተን መብታቸው የተጠበቀ ነው።

በ " ማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ፈተና ሳይፈተኑ የወጡ ተማሪዎች ፦

ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ (1,700 ተማሪዎች)
ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (1,226 ተማሪዎች)
ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (2,711 ተማሪዎች)
ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (7,356 ተማሪዎች) በድምሩ 12,993 ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተና ሳይጀምሩና የአንድ ቀን ሁለት ፈተና ከወሰዱ እንዲሁም የሁለት ቀን 4 ፈተናዎች ከወሰዱ በኃላ " አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች ከዚህ በኃላ በ " መደበኛ ተማሪነት " መፈተን #የማይችሉ ሲሆን በ2015 በግል መፈተን ይችላሉ።

- በታወቁ የጤናና ሌሎችም እክሎች ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈተናሉ።

- " የፈተናው ዉጤት " በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈተኑ ተማሪዎች በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሰረት ከተፈተኑ በኋላ የሁለቱንም ዉጤት ተጠቃሎ ይፋ ይደረጋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
2.7K viewsedited  12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 18:11:48
" ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ይገለጻል።"

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)


የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ወይም 98 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ያልወሰዱና በተለያዩ አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ እንዲሁም በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

በአራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ12 ሺህ በላይ ፈተናውን አንፈተንም ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ #እንደማይችሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ነገር ግን #በግል መፈተን ይችላሉ ብለዋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንደሚገለጽ ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
3.3K viewsedited  15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 12:18:00
የ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተናን #በግንቦት ወር ለመስጠትም ታቅዷል ፦ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስቴር በ " ኮቪድ-19 ወረርሽኝ " ምክንያት የተዛባውን የትምህርት ካላንደር በዘንድሮው ዓመት እንደሚያስተካክል ጠቁሟል።

" በ2015 ሁለት ፈተና ነው የምንሰጠው። አሁን የምንሰጠው ፈተና (ከመስከረም 30 ጀምሮ) የ2014ን ፈተና ነው።

ከኮቪድ ጊዜ ጀምሮ መርሀ ግብሩ እየተበላሽ በአጠቃላይ የትምህርት ስርዓታችን ግልፅ የሆነና ሁሉም የሚያውቀው የአካዳሚክ ካላንደር ሊኖረን አልቻለም ፤ እሱን በዚህ ዓመት እናስተካክላለን አሁን መስከረም 30 የምንሰጠው የ2014ን ነው ግንቦት ላይ የ2015 ተማሪዎችን እንፈትናለን።

ከዛ በኃላ ባሉት ጊዜያት የአካዳሚክ ካላንደሩ ከሞላ ጎደል ወደ ስርዓቱ ይገባል። "

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
2.9K viewsedited  09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 13:27:35
በፊሊፒንስ የሚገኝ ኮሌጅ ተማሪዎች ፈተና እንዳይኮራረጁ “ጭንቅላታችሁን ሸፍኑ” ማለቱ እያነጋገረ ነው

በፊሊፒንሷ ልጋዝፒ ከተማ የሚገኝ አንድ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኝ ኮሌጅ ተመሪዎች ወደጎናቸው አጮልቀዉ በመመልከት ፈተና እንዳይሰርቁ በማሰብ ጭንቅላታቸውን የሚሸፍን ነገር እንዲለብሱ ታዘዋል።

ይህንን ተከትሎም ተማሪዎች ካርቶኖችን፣ የእንቁላል መደርደሪያዎችን፣ የሞተር ሳይክል ሄልሜት እንዲሁም ከሌሎች የወዳደቁ ነገሮች በራሳቸው ፈጠራ የሰሯቸውን መሸፈኛዎች ለብሰው በፈተናው ላይ መገኘታውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በባይኮል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ ማንዳን፤ ተማሪዎች እንዳይኮራረጁ የተተገበረው አሰራር ውጤታማ እንደነበረ አስታውቀዋል።
በፈተና ወቅት ፊት መሸፈን እንዲተገበር ያነሳሳቸው ከዓመታት በፊት በታይላንድ ውስጥ ተተግብሮ ያዩት አንደሆነም ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ ተናግረዋል።
በፈረንጆጁ 2013 ላይ የባንኮክ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፈተና ላይ በሚቀመጡበት ወቅት በግራና በቀኝ በኩል ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ በወረቀት እንዲሸፍኑ በማድረግ ፈተና እንዲፈተኑ ተደርጎ ነበር።

ከዚህ በመነሳት “የፀረ ኩረጃ ኮፍያ” በባይኮል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ መተግበሩንም ፕሮፌሰሯ አስታውቀዋል።
ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ፤ ጥብቅ የፈተና ቁጥጥር ተማሪዎች ለማጥናት አነሳስቷል ያሉ ሲሆን፤ ይህም የተሸለ አፈጻጸም ማስገኘቱንም ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት በርካቶች ፈተናቸውን በአግባቡ እና በተሰጣቸው ጊዜ ማጠናቀቃቸውን የገለጹት ፕሮፌሰሯ፤ ፈተና ሲሰርቅ የተያዘ ተማሪ እንደሌለም አስታውቀዋል።

#አልዓይን

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
2.8K viewsedited  10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-21 12:28:32
ፈተናው ተጠናቋል

ላለፉት አራት ቀናት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተጠናቋል።

ዛሬ ጠዋት የተሰጠውን የሥነ ዜጋና ሥነምግባር ትምህርት ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው መመለስ ጀምረዋል (በተለይ በቅርብ ርቀት የሚገኙ።)

ተማሪዎቹ በተዘጋጀላቸው ትራንስፖርት ወደየመጡበት እየተሸኙ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ነው።

ምስል፦ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
3.4K viewsedited  09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 10:37:30
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ፈተናው እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ መሰጠት ይቀጥላል።

በሌላ በኩል ፤ ከትላንት ከእኩለ ቀን አንስቶ የተገደበው የቴሌግራም አገልግሎት ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ ነው።

ቴሌግራም ኢትዮጵያ ባሉት በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እየሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል።

የቴሌግራም መገደብን በተመለከተ ማብራሪያ የሚሰጥ አካል ባይኖርም ከዚህ ቀደም በነበሩት የብሔራዊ ፈተና ቀናት / በባለፈው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ወቅትም (ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ፈተናቸውን እስኪፈተኑ ድረስ) ሲገደብ ነበር።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
3.5K viewsedited  07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ