Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education®

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education®
የሰርጥ አድራሻ: @tmihirt_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Student_Comment_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-12-04 08:33:20 ለቀጣይ ዙር የ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች;
።።።፡።።።።:::::
ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ እየተቃረበ መሆኑን አውቃችሁ በተዘጋጃችሁት ልክ ተረጋግታችሁ ለመስራት ጥረት እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በተለይ በግጭት አካባቢ የነበራችሁ ተማሪዎች በብዙ ችግር ውስጥ ሁናችሁ ስትዘጋጁ እንደቆያችሁ ይታወቃል። ችግራችሁን በመገንዘብም ቀጣዩ ዙር ፈተና የተዘጋጀላችሁ መሆኑን በመገንዘብ ዕድላችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት ምክራችንን እንለግሳለን።

በአንደኛው ዙር ፈተና (በተለይ በማህበራዊ ሳይንስ ፈተና) ወቅት የተከሰቱት ችግሮች እናንተንም እንዳይገጥሟችሁ ማስታወስ ተገቢ ነው ብዬ ስላሰብሁ የሚከተሉትን ላጋራችሁ ወደድሁ:

1. በ2013 ተፈትነው ነገር ግን በድጋሚ በመደበኛው ኘሮግራም ለመፈተን እድል የነበራቸው የተወሰኑ ተማሪዎች(ሁሉንም ለማለት አይደለም) ሲያጠኑ ስላልከረሙ እና የተሻለ ውጤት ማምጣት የማይችሉ መሆናቸውን በመገመት የፈተና ስርዓቱን ለማወክ ባደረጉት ሙከራ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው እና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ተስፋ የነበራቸው ተማሪዎቻችን ከፈተና ተስተጓጉለውብናል። ይህ ድድርጊት እጅግ በጣም ስሜታችንን ጎድቶት አልፏል። በመሆኑም በቀጣይ እንዳይደገም ትምህርት መውሰድ ተገቢ ነው።

2. አንዳንድ ተማሪዎች ፈታኞችን ያልተገባ ንግግር በመናገር እና በማበሳጨት እንዲሁም የክፍል ፈተና ስርዓቱ እንዲረበሽ በማድረግ ፈታኞች ፈተናውን በችግር እንዲመዘግቡት የማድረግ ያልተገባ ግፊትም ተስተውሏል።

ይህ ድርጊት ምንጩ አስከአሁን ግልፅ ባይሆንም በተለይ ፈታኞች በሳል ሁነው ችግሩን በጥበብ ማለፍ ካልቻሉ ተፅዕኖው ቀላል እንደማይሆን ስጋት መፍጠሩ አልቀረም።

በጊዜው ሁሉም ቦታ ለመድረስ ባይቻልም መድረስ በቻልንባቸው የፈተና ጣቢያዎች ፈታኞችን ለማረጋጋት እና ድርጊቱ ውስን ቁጥር ያላቸው የተለዬ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው በትዕግስት የፈተና ስርዓቱን እንዲመሩት ለማግባባት ተሞክሯል። ሌሎች ያልደረስንባቸው ጣቢያዎች ሁኔታ ምንይመስል እንደነበር ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ፈታኞች ይህን ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን በትዕግስት እና በጥበብ ተወጥተውት እና ለብዙሀኑ ተማሪዎች ሲባል የአንዳንድ ተማሪዎችን ያልተገባ ስነምግባር በትዕግስት አልፈውት እንደሚሆን እንጠብቃለን።

3. በተለይ ድብረታቦር ዩኒበርስቲ ላይ የተፈጠረው ያለመረጋጋት ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲፈተኑ የሚያስችል ሁኔታ ነበር ብሎ ለማለት ያስቸግራል። የነበረው ሁኔታ ፈተና አቋርጠው በሄዱት ላይ ብቻም ሳይሆን በፈተና ሂደቱ ውስጥ በነበሩት ተማሪዎች ላይም ተፅዕኖው ከባድ እንደሚሆን ይገመታል።

በዚህም ሁከት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ውጤታማ ተማሪዎቻችን ባላሰቡት መንገድ ተስተጓጉለውብናል።

በአጠቃላይ የመጀመሪያው ዙር ፈተና እንደሀገር የመጀመሪያ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ከትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ ከት/ቢሮውም በኩል የነበሩ ከቅድመዝግጅት መጓደለም ጋር የተያያዙት መለስተኛ ችግሮች (በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ወቅት ማስተካከያ የተደረገባቸው ችግሮች)ተጨምረውበት በርካታ ተማሪዎቻችን ከፈተና ስርዓቱ የተስተጓጎሉበት ሁኔታ መፈጠሩ የትምህርት ማህበረሰቡን እጅግ በጣም ያሳዘነ ክስተት ሆኗል።

የነበሩ የቅድመዝግጅት መጓደሎችን እና አጠቃላይ ሂደቱን በሚመለከት ለሚመለከተው አካል በጊዜው የግምገማ ሪፓርት ስላቀረብን እዚህ ላይ መዘርዘሩ አያስፈልግም።

በአጠቃላይ ከግምገማ ሪፓርታችንም ሆነ ከሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት ውሳኔ ሰጭው አካል የሚሰጠው ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣዩ ዙር ፈተና የባለፋት ችግሮች በድጋሜ እናንተንም እንዳያጋጥሟችሁ ተገቢውን የጥንቃቄ ቅድመዝግጅት እንድታደርጉ ከወዲሁ እያሳሰብሁ መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!
ማተብ ታፈረ(ዶ/ር)

የአብክመ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
692 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 19:48:40 English model exam with answer key

Number of Questions - 120

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
724 viewsedited  16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 16:03:15 የ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይፋ ይደረጋል።

የ 2014 የ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ከ 2ተኛው ዙር ተፈታኞች ውጤት ጋር በአንድ ላይ ይለቀቃል።

የ 2ኛ ዙር ፈተና ከ ታህሳስ 11-14 ይሰጣል። የ 2ኛ ዙር ፈተና እርማት አንድ ሳምንት ባልሞለ ውስጥ ታርሞ ተማሪዎች ውጤታቸውን ያውቃሉ።

በአጠቃላይ የ 2014 የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከጥር ወር ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረጋል።

አዲስ ነገር ካለ እናሳውቃለን።
Via #et_university

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.2K viewsedited  13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 12:12:13 ሀምሌ 26/2014 ዓ.ም በትምህርት ሚኒሰትሩ ፀድቆ ለትግበራ የተላከው የመውጫ ፈተና መመሪያ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
85 viewsedited  09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 06:48:52
የሁለኛው ዙር መፈተኛ ቀን ታወቀ!!!

በምዕራብ ሸዋ ዞን ባሉ 7 ወረዳዎች የመጀመሪያ ዙር ፈተና ያልተፈተኑ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ፈተና ቀን ታህሳስ 11 2015 እንደሆነ ዛሬ የሸዋ ዞን ትምህርት መመሪያ አረጋግጧል

ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ዩንቨርስቲዎች ከ ታህሳስ 7-9 ይጓጓዛሉ

የተማሪዎች ዉጤት ታህሳስ ወር መጨረሻ ሚገለጽ ይሆናል

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
2.0K viewsedited  03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 21:48:41
| የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)

• የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

• የመውጫ ፈተናው የመደበኛ፣ የማታ እና የርቀት መርሃ ግብር ተመራቂ ተማሪዎችን ይመለከታል።

• በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ ይደረጋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.5K viewsedited  18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 21:56:57
የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሥራ ማቆም አድማን ማን ጠራው?

በዩኒቨርሲቲዎች መምህራን የፊታችን ሰኞ ኅዳር 26 ቀን፣ ይደረጋል የተባለውን የሥራ ማቆም አድማ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች መምህራን እና ቴክኒክ ረዳቶች ማኅበር እንዳልጠራው አስታወቀ።

የኢትዮጵያ 42 ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አለማቅረቡን ፕሬዝዳንቱ ዶክተር በፍቃዱ ዘለቀ ዛሬ ለDW ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር በፍቃዱ እርሳቸው በሚመሩት ማኅበር ስም ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረቡት አስራ አራት ጥያቄዎች በእርግጥም ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች መሆናቸውን ለዶይቼ ቬለ ቢያረጋግጡም የሥራ ማቆም አድማ ግን እንዳልተጠራ ገልጸዋል። ማኅበሩ ይህንን ያደረጉት የማናውቃቸው የተደራጁ አካላት ናቸው ብሏል። ይህን ያደረጉ ያላቸውንም እንደሚከስ አሳውቋል።

በተቃራኒው ዶይቸ ቬሌ ያነጋገራቸው የዩኒቨርስቲ መምህራን የሥራ ማቆሙን አድማ ለማድረግ እንደውም ዘግይተናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበርን ስም እና ዓርማ በያዘ ደብዳቤ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ኅዳር 15 ቀን፣ 2014 ዓ.ም የተሰራጨው መግለጫ አስራ አራት ጥያቄዎችን የያዘ ነው። ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል የደመወዝ ጭማሪ፣ የደረጃ ዕድገት፣ የቤት አበልን የተመለከቱ ይገኙበታል። ደብዳቤው በተጨማሪ ሥራዎች የሚገኝ ገቢ ላይ የግብር ቅነሳ፣ የሦስተኛ ዲግሪ የምርምር ገንዘብ መጠን፣ የመምህራን የዝውውር ጉዳዮችን ጭምር ያካተተ ነው።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
455 viewsedited  18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 19:45:22 አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው

ለወጣ 500 ብር ካርድ
ለወጣ 250 ብር ካርድ
ለወጣ 100 ብር ካርድ

ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
241 views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 12:39:19 ትምህርት ሚንስቴር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዲጂታል ለመስጠት ታብሌቶችን አገር ውስጥ ለማስመረት እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ ማለቱን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሚንስቴሩ የመስሪያ ቤታቸውን የሥራ አፈጻጸም አስመልክተው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ፈተናውን በኢንተርኔት ለመስጠት በውጭ አገር የቴክኖሎጂ ባለሙያ ኢትዮጵያዊያን የሶፍትዌር ሥራዎችን እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑን ሚንስትር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል ተብሏል። ሚንስቴሩ ታብሌቶቹን አገር ውስጥ ለማሰራት የወሰነው፣ ታብሌቶቹን በውጭ ለመግዛት ዋጋቸው በመወደዱ እንደሆነ መግለጹን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
887 viewsedited  09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 07:13:39 ለ Pp የሚሆን ጥቅስ አጥተው ያውቃሉ? ወይስ ለፍቅረኛዎ የሚልኩት የፍቅር መልዕክት ይፈልጋሉ? ተቀላቀሉን
251 views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ