Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education®

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education®
የሰርጥ አድራሻ: @tmihirt_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Student_Comment_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-11-25 21:49:34 ለ Pp የሚሆን ጥቅስ አጥተው ያውቃሉ? ወይስ ለፍቅረኛዎ የሚልኩት የፍቅር መልዕክት ይፈልጋሉ? ተቀላቀሉን
65 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 11:44:36 የ ኪያ ቁጥር 2 ፊልም አዲሱ ማጀቢያ ሙዚቃ ዳውንሎድ ማድረግ ሳይጠበቅባቹ ከስር 'Play' ሚለው በመንካት ያዳምጡ

ኤሊያስ ተሾመ - ኪያዬ ቁ.2
Play ▷ ◉─────── 04:52
14 views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 19:50:29
የ12ኛ ክፍል ፈተና ላመለጣችሁ የሀዋሳ እና አካባቢዋ ተማሪዎች በሙሉ

"ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት አድርጉ"
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በተለያየ ምክንያት የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን በታህሳስ ወር መጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርይ መምሪያ አሳውቋል።
- በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በመሸጋገሪያ ድልድይ ተሰብሮ በደረሰው አደጋ ምክንያት የመጀመሪያውን ቀን ፈተና ያልተፈተኑ፤

- በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ፤

- የተለያየ ማህበራዊ ችግር አጋጥሟቸው ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል አሳውቀው ለፈተና ያልተቀመመጡ ፤

- በሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ፤ " ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች በታህሳስ ወር  2015 ዓ.ም  በመጀሪያ ሳምንት አከባቢ ፈተናው ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው " ያለ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አውቀው ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
886 views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 19:49:45
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይገለጻል?

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል።

ሚኒስቴሩ በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ሰምተናል።

አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ከሁለተኛ ዙር ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Via : tikvah

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
849 viewsedited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 12:05:28 የ ኪያ ቁጥር 2 ፊልም አዲሱ ማጀቢያ ሙዚቃ ዳውንሎድ ማድረግ ሳይጠበቅባቹ ከስር 'Play' ሚለው በመንካት ያዳምጡ

ኤሊያስ ተሾመ - ኪያዬ ቁ.2
Play ▷ ◉─────── 04:52
1.1K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 22:11:47
የ2015  የዩንቨርስቲ  መሙያ ፎርም ይህን ይመስላል

በዚህም  40 ዩንቨርስቲዎች  ለምርጫ  ተቀምጠዋል

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
3.0K viewsedited  19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 13:13:41
"የተሰረቀና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰጥበት የትምህርት ስርዓት ይዘን መቀጠል አንችልም " ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
................................................

በ31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ላይ እየተደረገ ባለው ውይይት በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

አራተኛ ክፍል ደርሶ ማንበብ የማይችል ተማሪ እንዲሁም የተሰረቀና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰጥበት የትምህርት ስርዓት ይዘን መቀጠል አንችልም ያሉት ሚኒስትሩ ለአንዴና ለመጨረሻ የትምህርት ስርዓቱን ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

ችግሮቹን ደረጃ በደረጃ ለይቶ በመፍታት ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ማፍራት እንደሚገባም አብራርተዋል ።

እንደ ትምህርት ማህበረሰብ በቀጣይ አራት ዓመት መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት መሥራት ይኖርብናል በማለት ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የትምህርት ዘርፍ አመራር፣ ባለድርሻ አካላት እና የህዝቡን ትብብር እንፈልጋለን ብለዋል።

በተለይም ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ በማጥራት መሥራት የምንፈልገውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እንተገብራለን ያሉ ሲሆን በዚህም ወደ ኋላ የምንልበት ሁኔታ የለም በማለት ተናግረዋል ።

በትምህርት ሴክተሩ መሥራት ያለብንን ለዛሬ ሳይሆን ለነገው አስበን እንስራ ይህንንም ማድረግ እንችላለን በማለት ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል ።

በዚህ የትምህርት ጉባኤ የትምህርት ስርዓቱን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
579 views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 06:30:04 "የሚቀጥሉት አራት ዓመታት የመንግስት የትምህርት ዘርፍ ትኩረት ከመዋዕለ ህጻናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ አስተማማኝ መሰረት መጣል ይሆናል።"

ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከስምንት እስከ አስር ሺህ የሚጠጉ የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል።

"በርከት ያሉ የመጀመሪያ ደረጃ እና በርከት ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገንብተናል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቀዳማዊት ዕመቤት ጽ/ቤት ብቻ 28 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ገንብቷል ብለዋል።

"የነገሮች ሁሉ መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ነው" ሲሉ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ዩኒቨርሲቲዎችን ከመክፈት ይልቅ ለታችኛው የትምህርት ደረጃ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የተማሪዎች ምገባን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ 9.5 ሚሊዮን ህጻናትን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ መቻሉን አመልክተዋል።

"ይህም አሀዝ የአንዳንድ አገራት ህዝብ ቁጥር እንደማለት ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

"የምገባ ፕሮግራሙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው" ብለዋል።

"ታዳጊ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው በዳቦ ምክንያት ተስተጓጉለው እንዳይቀሩ እንደሀገር አበክረን ልንሰራ ይገባል" ብለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.1K viewsedited  03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 06:30:04
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት እስከ ሦሥት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ገለጹ።

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሦሥት ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ራስ ገዝ ሆኖ ከመንግስት ዩኒቨርሲቲ ምድብ ይወጣል ብለዋል።

"አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተከትሎ ባህር ዳር፣ ሀራማያ፣ ጅማ፣ መቐለ፣ ሀዋሳ ... የመሳሰሉት ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች በፍጥነት ከመንግስት በጀት ወጥተው ራስ ገዝ (Autonomous) መሆን አለባቸው" ብለዋል።

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ መንግስት አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.1K viewsedited  03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 20:48:02 ለ Pp የሚሆን ጥቅስ አጥተው ያውቃሉ? ወይስ ለፍቅረኛዎ የሚልኩት የፍቅር መልዕክት ይፈልጋሉ? ተቀላቀሉን
239 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ