Get Mystery Box with random crypto!

'የተሰረቀና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰጥበት የትምህርት ስርዓት ይዘን መቀጠል አንችልም ' ፕ | Ministry of education®

"የተሰረቀና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰጥበት የትምህርት ስርዓት ይዘን መቀጠል አንችልም " ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
................................................

በ31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ላይ እየተደረገ ባለው ውይይት በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

አራተኛ ክፍል ደርሶ ማንበብ የማይችል ተማሪ እንዲሁም የተሰረቀና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰጥበት የትምህርት ስርዓት ይዘን መቀጠል አንችልም ያሉት ሚኒስትሩ ለአንዴና ለመጨረሻ የትምህርት ስርዓቱን ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

ችግሮቹን ደረጃ በደረጃ ለይቶ በመፍታት ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ማፍራት እንደሚገባም አብራርተዋል ።

እንደ ትምህርት ማህበረሰብ በቀጣይ አራት ዓመት መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት መሥራት ይኖርብናል በማለት ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የትምህርት ዘርፍ አመራር፣ ባለድርሻ አካላት እና የህዝቡን ትብብር እንፈልጋለን ብለዋል።

በተለይም ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ በማጥራት መሥራት የምንፈልገውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እንተገብራለን ያሉ ሲሆን በዚህም ወደ ኋላ የምንልበት ሁኔታ የለም በማለት ተናግረዋል ።

በትምህርት ሴክተሩ መሥራት ያለብንን ለዛሬ ሳይሆን ለነገው አስበን እንስራ ይህንንም ማድረግ እንችላለን በማለት ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል ።

በዚህ የትምህርት ጉባኤ የትምህርት ስርዓቱን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER