Get Mystery Box with random crypto!

'የሚቀጥሉት አራት ዓመታት የመንግስት የትምህርት ዘርፍ ትኩረት ከመዋዕለ ህጻናት እስከ ሁለተኛ ደረ | Ministry of education®

"የሚቀጥሉት አራት ዓመታት የመንግስት የትምህርት ዘርፍ ትኩረት ከመዋዕለ ህጻናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ አስተማማኝ መሰረት መጣል ይሆናል።"

ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከስምንት እስከ አስር ሺህ የሚጠጉ የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል።

"በርከት ያሉ የመጀመሪያ ደረጃ እና በርከት ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገንብተናል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቀዳማዊት ዕመቤት ጽ/ቤት ብቻ 28 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ገንብቷል ብለዋል።

"የነገሮች ሁሉ መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ነው" ሲሉ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ዩኒቨርሲቲዎችን ከመክፈት ይልቅ ለታችኛው የትምህርት ደረጃ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የተማሪዎች ምገባን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ 9.5 ሚሊዮን ህጻናትን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ መቻሉን አመልክተዋል።

"ይህም አሀዝ የአንዳንድ አገራት ህዝብ ቁጥር እንደማለት ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

"የምገባ ፕሮግራሙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው" ብለዋል።

"ታዳጊ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው በዳቦ ምክንያት ተስተጓጉለው እንዳይቀሩ እንደሀገር አበክረን ልንሰራ ይገባል" ብለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER