Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education®

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education®
የሰርጥ አድራሻ: @tmihirt_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Student_Comment_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-10-05 18:41:17
#MoE

የእስልምና እምነት ተከታይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የመውሊድ በዓልን አክብረው መስከረም 29/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ይችላሉ ተብሏል።

ይሁን እንጂ መስከረም 28/2015 ዓ.ም የመውሊድ በዓል መሆኑን ተከትሎ፤ የእስልምና እምነት ተከታይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በዓሉን አክብረው መስከረም 29/2015 ዓ.ም መግባት እንዲችሉ የተፈቀደላቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በዚህም ተፈታኞቹ እሁድ መስከረም 29/2015 ዓ.ም ጠዋት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በመግባት ከሰዓት ስለፈተናውና ተያያዥ ጉዳዮች በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ገለጻ እንደሚደረግላቸው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
877 viewsedited  15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 12:15:15
የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈትኑ መምህራንን ምደባ አካሂዷል።

መምህራኑ ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት የተመደቡ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ሚቀርቡ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎችን እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 260/2004 አንቀፅ 9(2) በተሰጠው ስልጣንና በሀገር አቀፍ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2012 መሰረት ፈተና ለመፈተን ወደ ሌላ መፈተኛ ማዕከል የተመደበ መምህር በተዘጋጀው የፈተና አሰጣጥ እና አፈጻጸም ማንዋል 01/2014 መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ወደ ተመደበበት ቦታ የመገኘት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ይገልጻል፡፡

በመመሪያው መሰረት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተመደቡበት አካባቢ ሄደው የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት የመወጣት ግዴታ ያለባቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከጉዞ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ማንኛውንም ጥያቄ እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ከወዲሁ እያሳወቁ ይገኛሉ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ትላንት በሰጡት መግለጫ፤ " ከዚህ በፊት የነበረውን የኔ አካባቢ ሰው፣ የኔ ዘመድ የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም " ሲሉ ተናግርዋል።

(ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከፈታኝ መምህራን ምደባ ጋር በተያያዘ ማንኛውም አይነት ጥያቄ እንደማያስተናግድ ያሳወቀበት ነው።)

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.1K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 15:12:32
በቅርቡ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ባለፉት ዓመታት የተከሰቱ የፈተና ደንብ ጥሰቶች እና ማጭበርበሮች እንዳይደገሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

ተማሪዎች በሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እና በፈተና ጣቢያዎች አካባቢ ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚደረግ
የአገልግሎቱ ም/ዋ/ዳይሬክተር ይልቃል ወንድሜነህ ገልጸዋል።

ፈተና ወረቀቶቹን ወደ ፈተና ጣቢያዎች ከማጓጓዝ ጀምሮ ከፍተኛ ጥበቃ እንደሚደረግ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።

ባለፈው ዓመት የተፈጠረው አይነት የኅትመት ላይ ስህተት እና ማጭበርበር እንዳይፈጸም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የጥንቃቄ ሥራ መከናወኑንም ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች ወደ ፈተና ቦታዎች ሲመጡ ስልክም ሆነ መሰል የኤልክትሮኒክስ መሳርያዎች እንዳልተፈቀደ የተናገሩት ም/ዋ/ዳይሬክተሩ፤ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት በየመጡበት ወረዳ ተወክሎ በሚመጣ አካል እና ግቢ ውስጥ ባሉ የመገናኛ ዜዴ አማራጮች እንደተቀመጡ ጠቁመዋል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም ይሰጣል። #አሚኮ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.3K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 10:52:57 ፈተናው ተሰረቀ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተሰርቋል  ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት  Join የሚለውን ይጫኑ
1.2K views07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 21:18:40
በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና በ10 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ 31 ማዕከላት ይሰጣል፡፡

ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በክልሉ ሁሉም የመፈተኛ ተቋማት እና ማዕከላት በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ምክትል ኮሚሽነር እንየው ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ወረዳን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቀመጠው ጊዜ ለማድረስ በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ዝግጅት ማድረጉን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ውቤ አጥናፉ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች የወረዳ ትራንስፖርት ቢሮ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሰረት በጊዜ እየተገኙ እንዲስተናገዱ ጠይቀዋል፡፡

ሀገራዊ ግዴታቸውን በአግባቡና በሀላፊነት የማይወጡ የትራንስፖርት ማህበራትና ባለሀብቶች በትራንስፖርት መመሪያ እና በሕግ ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በሚጓጓዙባቸው ቀናት መደበኛ ትራንስፖርት ስለማይኖር ሕዝቡ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንዲተባበር ጥሪ አድርገዋል፡፡ #አሚኮ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
559 viewsedited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 21:18:40
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

ፌደራል ፖሊስ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመቀናጀት ብሔራዊ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።

ፈተናው ከማንኛውም የፀጥታ ችግር ነፃ ሆኖ ተፈታኞች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው መፈተን እንዲችሉ የፀጥታ መዋቅሩ ፈተናውን አጅቦ ለማጓጓዝ እና ጠንካራ ፍተሻዎችን ለማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጉን
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገልጸዋል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
500 views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 16:11:55 ፈተናው ተሰረቀ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተሰርቋል  ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት  Join የሚለውን ይጫኑ
1.1K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 15:38:28
ፈተናው በ13 የትምህርት አይነቶች በ12 የኮድ ስብጥር መዘጋጀቱን ዶ/ር ስለሺ ከበደ ዛሬ አረጋግጠዋል ።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.3K viewsedited  12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 12:27:22
ዘንድሮ ከ900,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ዓመታት ከፈተና ስርቆትና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ችግር ገጥሞት የነበረ መሆኑን ገልጾ ዘንድሮ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተፈታኞች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲፈተኑ እንደሚደረግ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብሏል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅት #መጠናቀቁንም ሚ/ሩ አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ዘንድሮ ከ900,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና የሚቀመጡ በመሆኑ ይህንን ቁጥር በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ባለመቻሉ በሁለት ዙር ፈተናው እንደሚሰጥ አስረድቷል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26-28 ወደሚፈተኑባቸው ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 02 ፈተና ወስደው ከጥቅምት 03 ጀምሮ ወደመጡበት እንደሚመለሱ ተጠቅሷል።

በ2ኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 5 አስከ ጥቅምት 6 ወደ ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከጥቅምት 8 እስከ ጥቅምት 11 ፈተና የሚወስዱ ይሆናል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እና ሌሎችም ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶችን መያዝ እንደማይችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላምና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅላቸው ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን ኢብኮ ዘግቧል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.4K viewsedited  09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 11:32:37
ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፦

(ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር)

- በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላም እና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉ እና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ #ሁለተኛ ዙር ፈተና ይዘጋጅላቸዋል።

- አሁን ለፈተና ለማይቀመጡ 56 ሺህ ተማሪዎች በአንድ ወር ውስጥ ለፈተናው እንዲቀመጡ ይደረጋል።

- ከመስከረም 30 ጀምሮ የሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት እና ህትመት በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

- ተማሪዎችን ወደ ተመደቡባቸው አካባቢዎች የሚያደርሷቸው የክልል የፀጥታ አካላት ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲዎች የጥበቃና ፍተሻ ስራን የሚሰሩት #የፌዴራል_ፖሊሶች ናቸው።

#WMCC / #ኢብኮ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.4K viewsedited  08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ