Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈትኑ መምህራንን ምደባ አካሂዷል። መምህራኑ | Ministry of education®

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈትኑ መምህራንን ምደባ አካሂዷል።

መምህራኑ ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት የተመደቡ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ሚቀርቡ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎችን እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 260/2004 አንቀፅ 9(2) በተሰጠው ስልጣንና በሀገር አቀፍ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2012 መሰረት ፈተና ለመፈተን ወደ ሌላ መፈተኛ ማዕከል የተመደበ መምህር በተዘጋጀው የፈተና አሰጣጥ እና አፈጻጸም ማንዋል 01/2014 መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ወደ ተመደበበት ቦታ የመገኘት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ይገልጻል፡፡

በመመሪያው መሰረት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተመደቡበት አካባቢ ሄደው የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት የመወጣት ግዴታ ያለባቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከጉዞ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ማንኛውንም ጥያቄ እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ከወዲሁ እያሳወቁ ይገኛሉ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ትላንት በሰጡት መግለጫ፤ " ከዚህ በፊት የነበረውን የኔ አካባቢ ሰው፣ የኔ ዘመድ የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም " ሲሉ ተናግርዋል።

(ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከፈታኝ መምህራን ምደባ ጋር በተያያዘ ማንኛውም አይነት ጥያቄ እንደማያስተናግድ ያሳወቀበት ነው።)

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER