Get Mystery Box with random crypto!

በቅርቡ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ባለፉት ዓመታት የተከሰቱ የፈተና ደንብ ጥሰቶች እና | Ministry of education®

በቅርቡ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ባለፉት ዓመታት የተከሰቱ የፈተና ደንብ ጥሰቶች እና ማጭበርበሮች እንዳይደገሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

ተማሪዎች በሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እና በፈተና ጣቢያዎች አካባቢ ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚደረግ
የአገልግሎቱ ም/ዋ/ዳይሬክተር ይልቃል ወንድሜነህ ገልጸዋል።

ፈተና ወረቀቶቹን ወደ ፈተና ጣቢያዎች ከማጓጓዝ ጀምሮ ከፍተኛ ጥበቃ እንደሚደረግ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።

ባለፈው ዓመት የተፈጠረው አይነት የኅትመት ላይ ስህተት እና ማጭበርበር እንዳይፈጸም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የጥንቃቄ ሥራ መከናወኑንም ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች ወደ ፈተና ቦታዎች ሲመጡ ስልክም ሆነ መሰል የኤልክትሮኒክስ መሳርያዎች እንዳልተፈቀደ የተናገሩት ም/ዋ/ዳይሬክተሩ፤ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት በየመጡበት ወረዳ ተወክሎ በሚመጣ አካል እና ግቢ ውስጥ ባሉ የመገናኛ ዜዴ አማራጮች እንደተቀመጡ ጠቁመዋል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም ይሰጣል። #አሚኮ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER