Get Mystery Box with random crypto!

ዘንድሮ ከ900,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ዓመታት | Ministry of education®

ዘንድሮ ከ900,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ዓመታት ከፈተና ስርቆትና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ችግር ገጥሞት የነበረ መሆኑን ገልጾ ዘንድሮ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተፈታኞች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲፈተኑ እንደሚደረግ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብሏል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅት #መጠናቀቁንም ሚ/ሩ አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ዘንድሮ ከ900,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና የሚቀመጡ በመሆኑ ይህንን ቁጥር በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ባለመቻሉ በሁለት ዙር ፈተናው እንደሚሰጥ አስረድቷል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26-28 ወደሚፈተኑባቸው ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 02 ፈተና ወስደው ከጥቅምት 03 ጀምሮ ወደመጡበት እንደሚመለሱ ተጠቅሷል።

በ2ኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 5 አስከ ጥቅምት 6 ወደ ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከጥቅምት 8 እስከ ጥቅምት 11 ፈተና የሚወስዱ ይሆናል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እና ሌሎችም ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶችን መያዝ እንደማይችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላምና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅላቸው ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን ኢብኮ ዘግቧል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER