Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education®

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education®
የሰርጥ አድራሻ: @tmihirt_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Student_Comment_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-10-17 13:58:03
ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2014 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከዛሬ ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

ተፈታኞቹ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ በትምህርት ሚኒስቴር የወጣ መርሃ ግብር ያሳያል።

ተፈታኞቹ ለአራት ቀናት የሚቆየውን ብሔራዊ ፈተና መውሰድ ከመጀመራቸው በፊት ሰኞ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ ( ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል።

ፈተናው ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ተፈታኞች ጥቅምት 12 እና 13/2015 ዓ.ም ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

ባለፈው ሳምንት በተሰጠው የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና ከ586 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
2.9K viewsedited  10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 11:40:54
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና የጊዜ ሰሌዳ

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር በተገለጸዉ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዙር ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ያለምንም ችግር ተሰጥቶ ተጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በነዚሁ ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ድረስ ፈተና ይወስዳሉ።

የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ተፈታኞች የጊዜ ሰሌዳም፦

1. ጥቅምት 6 እና 7/2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

2. ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ ( ኦሬንቴሽን) ለተፈታኞች ይሰጣል።

3. ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናው ይሰጣል።

4.ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደ አካባቢያቸው ይመለሳሉ።

መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
5.0K viewsedited  08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 07:44:45
ያጋጥማል

ቀጣይ ለምትፈተኑ ይጠቅማችኃል

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
3.4K viewsedited  04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 19:40:04
የ2014 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የጊዜ ሰሌዳ፦

➤ ጥቅምት 05 እና 06/2015 ዓ.ም
      ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

➤ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም
     ገለጻ ( ኦሬንቴሽን) ለተፈታኞች ይሰጣል።

➤ ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም
     ፈተናው ይሰጣል።

➤ ጥቅምት 12 እና 13/2015 ዓ.ም
      ተፈታኞች ወደ አካባቢያቸው ይመለሳሉ።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
3.9K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 19:39:22
የመጀመሪያ ዙር ፈተና የወሰዱ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወደየአካባቢያቸው በመመለስ ላይ ናቸው።
-----------------
የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ ተፈታኞች ከየተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ወደየአካባቢያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

ዩኒቨርስቲዎችም መልካም ጉዞ በመመኘት ተማሪዎችን እየሸኙ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴርም ተማሪዎች በሰላም ወደየአካባቢያቸው እንዲመለሱ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

የመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በትላንትናው እለት የተጠናቀቀ ሲሆን የሁለተኛ ዙር ተፈታኞችም ከ ጥቅምት 5 /2015 ዓም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ይገባሉ።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
2.7K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 10:58:10
#Update

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

ይኸው የፈተና መርሀ ግብር ዛሬ ከሰዓት በኃላም ይቀጥላል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና መርሀግብር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ነገ ጥቅምት 2 / 2015 የሚጠናቀቅ ሲሆን ተማሪዎች ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 4 ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

በሌላ በኩል ፤ ትላንት የድልድይ መደርመስ አደጋ ደርሶ የአንድ ተማሪ ህይወት በጠፋበት እና በርካታ ተማሪዎች በተጎዱበት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ተነግሯል።

የደቡብ ክልል ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሀዋሳ ዋናው ግቢ ብሄራዊ ፈተና እየተሰጠ መሆኑን ገልጾ ሁሉም በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ ነው ብሏል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የፈተናውን ሂደት እየተመለከቱ መሆኑ ተነግሯል።

#Tikvah
@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.2K viewsedited  07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 21:19:41 አደይ ምዕራፍ ሁለት ክፍል 16 በይ ፉተለቆል ይከታተሉ
85 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 18:27:58
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቆ ተማሪዎች ለቀጣዩ ቀን ፈተና እየተዘጋጁ መሆኑን አሳውቋል።

በዛሬዉ እለት የተጀመረዉ 12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዕለት ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የገለፀው ሚኒስቴሩ " ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከተፈጠረዉ አሳዛኝ ክስተት እና በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ፈተና ሳይፈተኑ ከወጡ ተማሪዎች ሪፖርት ዉጪ አጠቃላይ ሂደቱ የተሳካ ነበር " ብሏል።

ፈተናው በመላው ሀገሪቱ ካሉት 130 የፈተና ጣቢያዎች በ128ቱ ጣቢያዎች ላይ ነበር ሲሰጥ የዋለው።

ትምህርት ሚኒስቴር የዛሬውን ፈተና ያጠናቀቁ ተማሪዎች በነገው ዕለት ለሚኖራቸዉ የሁለተኛ ቀን ፈተና ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጿል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
757 viewsedited  15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 10:46:58
#መግለጫ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና ሂደቱን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

- በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት " #አንፈተንም " በሚል ለቀው ወጥተዋል፤ ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለፃል።

- በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል።

- ከተጠቀሱት (ሀዋሳ እና መቅደላ አምባ) አካባቢዎች #በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ ነው።

#ENA

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.1K viewsedited  07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 10:35:00
ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው፦ ትምህርት ሚኒስቴር
**

በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተረጋጋ እና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመር እና አጠቃላይ ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም 130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተረጋጋ እና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን አብራርተዋል።

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ በምሥራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት "አንፈተንም" በሚል ለቀው መውጣታቸውን ገልጸው ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለጻል ብለዋል።

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ መጠነኛ መድረሱንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ተማሪዎች ኀዘናቸውን ገልጸው፣ የአደጋው ሰለባዎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

በአደጋው ጉዳት የገጠማቸው ተማሪዎች ከአገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል።

ከተጠቀሱት አካባቢዎች በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ግን ፈተናው በሰላም እና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
914 viewsedited  07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ