Get Mystery Box with random crypto!

#Update ትምህርት ሚኒስቴር የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቆ ተማሪዎች ለቀጣዩ ቀ | Ministry of education®

#Update

ትምህርት ሚኒስቴር የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቆ ተማሪዎች ለቀጣዩ ቀን ፈተና እየተዘጋጁ መሆኑን አሳውቋል።

በዛሬዉ እለት የተጀመረዉ 12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዕለት ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የገለፀው ሚኒስቴሩ " ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከተፈጠረዉ አሳዛኝ ክስተት እና በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ፈተና ሳይፈተኑ ከወጡ ተማሪዎች ሪፖርት ዉጪ አጠቃላይ ሂደቱ የተሳካ ነበር " ብሏል።

ፈተናው በመላው ሀገሪቱ ካሉት 130 የፈተና ጣቢያዎች በ128ቱ ጣቢያዎች ላይ ነበር ሲሰጥ የዋለው።

ትምህርት ሚኒስቴር የዛሬውን ፈተና ያጠናቀቁ ተማሪዎች በነገው ዕለት ለሚኖራቸዉ የሁለተኛ ቀን ፈተና ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጿል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER