Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና የጊዜ ሰሌዳ የ1 | Ministry of education®

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና የጊዜ ሰሌዳ

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር በተገለጸዉ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዙር ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ያለምንም ችግር ተሰጥቶ ተጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በነዚሁ ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ድረስ ፈተና ይወስዳሉ።

የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ተፈታኞች የጊዜ ሰሌዳም፦

1. ጥቅምት 6 እና 7/2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

2. ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ ( ኦሬንቴሽን) ለተፈታኞች ይሰጣል።

3. ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናው ይሰጣል።

4.ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደ አካባቢያቸው ይመለሳሉ።

መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER