Get Mystery Box with random crypto!

ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2014 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ የ12 | Ministry of education®

ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2014 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከዛሬ ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

ተፈታኞቹ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ በትምህርት ሚኒስቴር የወጣ መርሃ ግብር ያሳያል።

ተፈታኞቹ ለአራት ቀናት የሚቆየውን ብሔራዊ ፈተና መውሰድ ከመጀመራቸው በፊት ሰኞ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ ( ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል።

ፈተናው ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ተፈታኞች ጥቅምት 12 እና 13/2015 ዓ.ም ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

ባለፈው ሳምንት በተሰጠው የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና ከ586 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER