Get Mystery Box with random crypto!

ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው፦ ትምህርት | Ministry of education®

ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው፦ ትምህርት ሚኒስቴር
**

በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተረጋጋ እና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመር እና አጠቃላይ ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም 130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተረጋጋ እና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን አብራርተዋል።

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ በምሥራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት "አንፈተንም" በሚል ለቀው መውጣታቸውን ገልጸው ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለጻል ብለዋል።

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ መጠነኛ መድረሱንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ተማሪዎች ኀዘናቸውን ገልጸው፣ የአደጋው ሰለባዎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

በአደጋው ጉዳት የገጠማቸው ተማሪዎች ከአገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል።

ከተጠቀሱት አካባቢዎች በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ግን ፈተናው በሰላም እና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER