Get Mystery Box with random crypto!

#Update ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ድልድዩ የፈረሰው መሸከም ከሚችለው በላይ ተማሪ ወጥቶበት መሆኑን ገ | Ministry of education®

#Update

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ድልድዩ የፈረሰው መሸከም ከሚችለው በላይ ተማሪ ወጥቶበት መሆኑን ገልጿል።

ዩንቨርስቲው ይህ የገለፀው ባወጣው መግለጫ ነው።

" ዛሬ ጥዋት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲሸጋገሩ ሁለቱን ግቢዎች የሚያገናኘው ድልድይ ላይ ድልድዩ መሸከም ከሚችለው አቅም በላይ ተማሪዎች ሲወጡበት በመውደቁ አደጋ አጋጥሟል " ብሏል ዩኒቨርስቲው።

" በዚህ አደጋ ምክንያት ጥቂት ተማሪዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል " ያለው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጿል።

የዛሬውን ፈተናው መፈተን ያልቻሉ ተማሪዎች ሌላ ዕድል ከት/ት ሚኒስቴርና የፈተናዎች ድርጅት ጋር በመነጋገር እንደሚመቻችላቸውም አሳውቋል።

ፎቶ ፦ ክብሩ ግዛቸው

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER