Get Mystery Box with random crypto!

የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል ***** የመጀመሪያው ዙር | Ministry of education®

የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል
*****

የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከዛሬ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም አንስቶ መሰጠት ይጀምራል።

በመጀመሪያው ዙር ፈተናውን የሚወስዱት የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ፈተናው ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መርሐ-ግብር አመላከቷል።

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተፈታኞቹን ተቀብለው ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER