Get Mystery Box with random crypto!

ማሳሳቢያ:- ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች! ተፈታኞቻችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል፡፡ የተከለከሉ | Ministry of education®

ማሳሳቢያ:- ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች!

ተፈታኞቻችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል፡፡ የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ ድርጊቱ ከፍተኛ የፈተና ደንብ ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER