Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education®

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education®
የሰርጥ አድራሻ: @tmihirt_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Student_Comment_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-08-18 15:50:10 በአዲስ አበባ ትምህርት መስከረም 9 ይጀምራል

በ2015 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሆኖ ይሰጣል ተባለ

የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሀገር አቀፍ ሆኖ ይሰጣል።

የ2015 ዓመት መደበኛ የትምህርት ዘመን መስከረም 9 ቀን እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በ2015 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ተናግረዋል።
በአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ላይ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ በ2014 የትምህርት ዘመን ላይ የተከናወነ ሲሆን አዲሱ ስረዓተ ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ በሁሉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ተግበራዊ ይሆናል።

በሌላ በኩል በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም በከፊል በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 የትምህርት ዘመን የሙከራ ትግበራ ከተከናወነ በኃላ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ ይደረገል።

በ2015 ዓመት የትምህርት ዘመን 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፣የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ እንዲሁም 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ የማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል ፡፡በ2015 የትምህርት ዘመን ላይ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲተገበር በተለይ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ እና ከዚህ ቀደም በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረም በጋራ መሰራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የመጽሀፍ ስርጭትን በተመለከተ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በተማሪዎች እጅ እንዲደርስ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ አበበ ቸርነት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
4.3K viewsedited  12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 13:43:09
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሣችሁ፡፡

ቡሄ በሉ.... ሆ...
ልጆች ሁሉ...
#መልካም_በዓል!
3.2K viewsedited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 12:41:10 በመላው ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ፈተናዎች እየተቃረቡ ነው

ታዲያ በዚህ ወቅት ተማሪዎችን እጅግ የሚያስጨንቁ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው

እንዴት አድርገን ለፈተናው እናጥና?

ያጠናነውንስ ላለመርሳት ምን ማድረግ አለብን?

የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው።

የትምህርት ባለሙያዎችን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን፣ የሥነ ምግብ ተመራማሪዎች፣ ውጤታማ ተማሪዎችን እንዲሁም የሥነ አእምሮ ባለሙያዎችን ይጠቅማሉ ያሏቸውን 12 ነጥቦች በ PDF እንደሚከተለው አቅርበንላቹሀል ተጠቀሙባቸው ሼር በማድረግም ሌሎች ተማሪዎች እንዲጠቀሙ የበኩላችሁን ድርሻ አበርክቱ ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
3.1K viewsedited  09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:10:30
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ታብሌቶች ካልደረሱ ሌሎች አማራጮች እንደሚጠቀም መንግስት አስታወቀ!!

በሚቀጥለዉ አመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች በወቅቱ ካልደረሱ ሌሎች ምርጫዎችን መንግስት ይከተላል-ጠ/ሚ አብይ

በ2015 ዓ.ም የሚሰጠዉ ሀገር አቀፍ ፈተናን ዲጂታል በሆነ መንገድ በኦንላይን ምዘናዉን ለመስጠት ታቅዶ እንደነበር ይታወሳል። ለዚህም 1ሚሊዮን የሚሆኑ ታብሌት ኮምፒውተሮች ወደ ሀገር ይገባሉ ተብሎም ነበር።

ጠ/ሚ አብይ ይህን በተመለከተ በሰጡት ማብራርያ ያለዉን ስርቆት ለማስቀረት ሲባል ፈተናዉን ዲጂታላያዝ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም 1ሚሊዮን ታብሌት ኮምፕዩተሮቹን ከቻይና መንግስት ጋር በመሆን ለማስገባት እየተሰራ እንደነበር አስታዉሰዋል። ሆኖም በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያትም አምራች ድርጅቱ ስራዉን በተያዘለት ግዜ ማጠናቀቅ አለመቻሉን አስታዉቀዋል።

በ2015 ለመስጠት የታቀደዉ ፈተናዉ ፤ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ ታብሌት ኮምፒውተሮቹ በተያዘላቸዉ ግዜ ከደረሱ ፈተናዉ ይሰጣል ብለዋል። ሆኖም ታብሌቶቹ በግዜዉ ካልደረሱ መንግሰት ሌሎች ምርጫዎችን እንደሚጠቀም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
282 viewsedited  11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:38:18
ክሮም የምትጠቀሙ በአስቸኳይ update አድርጉ

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል በክሮም ብሮዉዘሩ (chrome browser) ላይ ተጠቃሚዎችን ለከፍተኛ የሳይበር ጥቃት የሚያጋልጥ ክፍተት መገኘቱን ተከትሎ አስቸኳይ የክፍተት መሙያ አቅርቧል።

ኩባንያዉ ለክፍተቱ መሙያ የክሮም እትም #Chrome 103.0.5060.114 ያቀረበ ሲሆን ይህም ለማይክሮሶፍት ዊንዶዉስ ተጠቃሚዎች የሚሆን መሆኑ ጠቁሟል።

ይህ የደህንነት ማዘመኛ በጉግል ኩባንያ የቀረበለት ክፍተት ከዚህ በፊት ያልተለየ እና የመረጃ መንታፊዎች በተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚያስችላቸዉ መሆኑን ጉግል ይፋ አድርጓል።

ይህ ቀደሞ ያልተለየ የሳይበር ጥቃት አጋላጭ ክፍተት #zero_day_vulnerability በክሮም ብሮዉዘር ላይ ሲደርሰ የፈረንጆቹ 2022 ከገባ ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑም ታዉቋል።
በመሆኑም የክሮም ብሮዉዘር ተጠቃሚዎች የክፍተቱን አደገኛነት በመረዳት በአስቸኳይ የመረጃ ማፈላለጊያዉን እንዲያዘምኑ ጉግል መክሯል።

Via: —INSA

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
729 viewsedited  19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:27:01
በአማራ ክልል የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ለሦሥት ቀናት ይሰጣል ተብሏል።

በክልሉ ከ359 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ፈተናው በክልሉ በሚገኙ 5 ሺህ 395 ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ መምህራን ፈተናውን በመስጠት ይሳተፋሉ።

የ8ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር እና በሐረሪ ክልሎች ትላንት መሰጠት ጀምሯል።

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.2K viewsedited  07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 10:19:13
#AddisAbaba

የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ መሰጠት ጀምሯል።

ፈተናው ከዛሬ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሦሥት ቀናት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ማስታወቁ አይዘነጋም።

ከተማ ዐቀፍ ፈተናው በአዲስ አበባ በሚገኙ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ ሲሆን 1 ሺህ 800 ፈታኞች እና 450 ሱፐር ቫይዘሮች ፈተናውን እየተቆጣጠሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በዛሬው የፈተና ውሎ ጠዋት የአማርኛ እና እንግሊዘኛ ፈተናዎች እየተሰጡ ሲሆን ከሰዓት ሂሳብ እና ባዮሎጂ ፈተናዎች ይሰጣሉ።

በአጠቃላይ በከተማዋ ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.5K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 09:19:03
መልካም ፈተና

የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ዛራ ይጀምራል::

ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ ተመኘን !!

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.4K viewsedited  06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 12:42:37
9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች ነፃ የት/ም እድል

የቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት 8ኛ ክፍል ለሚገኙና የተሻለ ውጤት ያላቸውን 10 ወንድና 10 ሴት በድምሩ 20 ተማሪዎችን ስፖንሰር አድርጎ ማስተማር ይፈልጋል

በመሆኑም በተቀመጡት መስፈርቶች መሠረት ተማሪዎችን መልምላቹህ ከሰኔ 30-ሀምሌ 6/2014 ዓ.ም ድረስ እንድትልኩልን ስንል እናሳስባለን::

1.በት/ታቸው ጠንካራና የደረጃ ተማሪ ሆነው የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል የትምህርት ሪፖርት ካርድ ማቅረብ የሚችሉ

2.ተማሪዎች በቅ/ዮሴፍ ት/ቤት የሚሰጠውን ፈተና ማለፍ የሚችሉ ተማሪዎች ሲሆን

3.መስፈርቱን ያሟሉ ወንድ ተማሪዎች በቅዱስ ዮሴፍ ሴት ተማሪዎች ደግሞ በናዝሬት የልጃገረዶች ት/ቤት የሚማሩ ይሆናል::

በግል ት/ቤት በነጻ የሚማሩ አቅም የሌላቸው ተማሪዎች መረጃ ካመጡ መወዳደር ይችላሉ)

አ/አ ከተማ አስተዳደር ት/ም ቢሮ

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.9K viewsedited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 13:39:11
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል ?

የትምህርት ሚኒስቴር የብሄራዊ ፈተና መሰረቅንና ኩረጃን ለመከላከል ፈተናው በኦንላንይ መስጠት እስኪጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።

የፈተናውን አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ ለጊዜው በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም የ2014 ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 20 / 2015 ዓ/ም በኃላ እንደሚሰጥ መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም ፤ እስካሁን ድረስ የተቀየረም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለፀ አዲስ ነገር የለም።

ከትላንት ጀምሮ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፈተናው ሃምሌ እና ነሃሴ ላይ ነው የሚሰጠው እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ ያልታወቀና ሀሰተኛ በመሆኑ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ በጥናታችሁ ላይ እንድታተኩሩ ወላጆችም ልጆቻችሁ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እገዛችሁን እንድታጠናክሩ ይሁን።

እጅግ በርካታ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጆች የሚከታተሉት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጉዳይን በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር ውጭ የሚወጡ መረጃዎችን አምናችሁ አትቀበሉ። አንድን መረጃ ስትሰሙ ከትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን አረጋግጡ።

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
2.8K viewsedited  10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ