Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education®

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education®
የሰርጥ አድራሻ: @tmihirt_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Student_Comment_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-09-13 16:15:25
በኦሮሚያ ክልል ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀመር ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀምር የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ወርቅነህ ነጋሳ እንደገለጹት በክልሉ ትምህርት መጀመር የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋል።

የመምህራን ዝግጅት፣ የመማሪያ መጻሕፍት ማዘጋጀትና የትምህርት ቤቶች ዝግጅት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።

የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ይኸው ስራ እስከ መስከረም 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

በዚሁ የትምህርት ዘመን በክልሉ 11 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የገለጹት ዳይሬክተሩ በእስከ አሁኑ ሂደት የተማሪዎች ምዝገባ ከ95 በመቶ በላይ መጠናቀቁን አመልክተዋል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
4.7K viewsedited  13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 12:34:24
የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ።

ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው።

በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፦

- ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ ነው።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተመድበዋል። ምደባው ሲዘጋጅ በተቻለ መጠን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲመደቡ ተደርጓል። በአቅራቢያቸው ያለው ዩኒቨርሲቲ በመኝታ ወይም በመፈተኛ ክፍሎች ብዛት ውስንነት ካለበት ወደ ሌላ ዞንና ክልል የመሄድ ዕድል ይኖራል።

- ገጠር አካባቢዎች ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊገጥማቸው ስለሚችል ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ተማሪዎቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ ይጓጓዛሉ።

- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች በመፈተናቸው ምክንያት ግን ወደ ተማሪዎችም ሆነ ወደ ወላጆች የሚሄድ ወጪ አይኖርም።

- ተማሪዎቹ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንዲላመዱት ለማድረግ ሲባል ፈተናው ከሚጀመርበት ቀናት ቀደም ብለው ወደ ዩኒቨርሲቲው ይጓዛሉ። ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ ድምፅም ሆነ ምሥል የሚቀዳና የሚቀርፅ አሊያም ሌላ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው መግባት አይችሉም።

- በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኞችም በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያድሩ ለማድረግ ታቅዷል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
5.6K viewsedited  09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 11:46:00
የአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከላንደር ላይ ለውጥ አድርጓል።

ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈ ትእዛዝ መሰረት ዩኒቨርሲቲው በሙሉ ከመስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም  ለአስራ ሁለተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና አገልግሎት ስለሚዉሉ በአካዳሚክ ካላንደሩን ላይ ለዉጥ ማድረጉን ገልጿል።

በዚህም ፦

#1ኛ፥ ሁለተኛ አመትና ከዚያ በላይ የቅድመ  ምረቃ  ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 22 ቀን እና ጥቅምት 23 ቀን  2015 ዓ.ም 

#2ኛ፥ አዲስና ነባር የድህረምረቃ  ተማሪዎች ምዝገባ  ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም
#3ኛ፥ ትምህርት የሚጀመረዉ ሐሙስ ጥቅምት 24  ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

#4ኛ፥ በ2014 ዓ.ም የገቡ የአንደኛ አመት ተማሪዎች በአስራ ሁለተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ምክንያት የሁለተኛ ሰሚስተር ትምህርት ተቋርጦ መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከዩኒቨርስቲ ጊቢዎች እንዲወጡና ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም  ተመልሰው ጥቅምት 21 ቀን  2015 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀምሩ ገልጿል።

#ማሳሰቢያ : ዩኒቨርሲቲው ከላይ ከተገለጹት ቀናት ዉጭ ወደ ጊቢ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ አሳስቧል።

በተጨማሪ ከመስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም  እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲ ጊቢዎች የተገኘ ማንኛውም ተማሪ የዲስፕሊን ቅጣት እንደሚወሰድበት አሥጠንቅቋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ ! !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
3.8K viewsedited  08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 13:27:18
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎችን በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገለጸ

ከመስከረም 2015 ዓ.ም. መጨረሻ አንስቶ በሁለት ዙር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጓጓዙበትን የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች በመንግሥት እንደሚሸፈኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማስታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ መሆኑን አስታውቆ፣ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ለማከናወን የሚያስችለውን ወጪ ለመሸፈን ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድለት ንግግር ላይ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። ፈተናው በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ ! !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
4.7K viewsedited  10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 11:28:58 How old are you?
11.4K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 20:21:34 ትልቁን የ TIK TOK ቻናል ይቀላቀላሉ
349 views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 20:03:46
በጋምቤላ ክልል የ2014 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 79 ነጥብ 5 በመቶ ያህሉ ወደቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን ተገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ፦

አማካይ ውጤት ለወንዶች 48 በመቶ እና ለወንድ አካል ጉዳተኞች 46 በመቶ / ለሴቶች 44 በመቶ እና ለሴት አካል ጉዳተኞች 42 በመቶ እንዲሆን ተወስኗል።

ለፈተናው ከተቀመጡ አጠቃላይ 16 ሺህ 629 ተማሪዎች 7,395 ወንዶችና 5,843 ሴት ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል አልፈዋል።

በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተማሪዎች ካርድ ይሰጣል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ ! !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
847 viewsedited  17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 19:34:26
#አሳፋሪ_ተማሪዎች

የሂሳብ ዉጤታችን ወረደ በሚል ምክንያት አስተማሪያቸዉን ከዛፍ ጋር አስረው የደበደቡት ተማሪዎች

በህንድ ጃርክሃንድ ግዛት ዱምካ ት/ቤት ተማሪዎች የሂሳብ መምህራቸውን እና የትምህርት ቤቱን የአስተዳደር ሰራተኞች የ9ኛ ክፍል ፈተና ውጤታችን ላይ እንወያይበታለን በሚል ሰበብ ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ ከወሰዱ በኃላ ከዛፍ ላይ አስረው ድብደባ መፈጸማቸዉ ተሰምቷል። የተማሪዎቹ የቁጣ መነሻ የ9ኛ ክፍል ሒሳብ ፈተና መጥፎ ውጤት በማምጣታቸዉ የተነሳ መሆኑን ኢንዲያ ታይምስ ዘግቧል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ ! !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
916 viewsedited  16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 09:08:13
ከ1 ሺሕ 400 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የውጭ ትምህርት እድል እንደተመቻቸላቸው ሚኒስቴሩ አስታወቀ

በ2014 በጀት ዓመት ከ1 ሺሕ 400 በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የውጭ ትምህርት እድል እንደተመቻቸላቸው የትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

በትምህርት ሚኒስቴር የውጭ ትምህርት እድል ክፍል ኃላፊ ኤርዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ እንዳሉት፣ ሚኒስቴሩ በየዓመቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የውጭ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ከተለያዩ አገር መንግሥታት ጋር አብሮ ይሠራል።

ሙሉ የአዲስ ማለዳን ዘገባ ያንብቡ -> https://bit.ly/3D2IlSE

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ ! !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
668 viewsedited  06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 11:07:50 ትልቁን የ TIK TOK ቻናል ይቀላቀላሉ
652 views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ