Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education®

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmihirt_minister — Ministry of education®
የሰርጥ አድራሻ: @tmihirt_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.99K
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Student_Comment_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-09-28 09:21:26
አሳዛኝ ዜና

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
743 viewsedited  06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 07:34:43
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ!

            መልካም በአል !!
1.0K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 21:49:45
አደይ ድራማ ምዕራፍ 2 ክፍል6 በአቦል ቲቪ ተለቋል

https://t.me/+4rzL1Wg0GQ0zMzdk
344 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 16:41:36
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናዉን ለማስተግበር ከተቋቋመዉ ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክፍለ ከተማ የትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
320 viewsedited  13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 21:37:30
በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ

ለ12ኛ ክፍል ተፈታች ተማሪዎች የተዘጋጀ ሞዴል ፈተና ፕሮግራም

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
582 viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 19:39:45
ምዕራፍ 2 አደይን በጥራት ለመከታተል ሊንኩን በመንካት ተቀላቀሉን

https://t.me/+4rzL1Wg0GQ0zMzdk
https://t.me/+4rzL1Wg0GQ0zMzdk
876 views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 12:55:58 ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

¤ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።

¤ አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።

¤ ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

¤ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::

¤ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤

¤ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

¤ ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።

¤ በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።

ወቅቱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ፈተና ተመኘን

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
578 viewsedited  09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 20:55:09
ምዕራፍ 2 አደይን በጥራት ለመከታተል ሊንኩን በመንካት ተቀላቀሉን

https://t.me/+4rzL1Wg0GQ0zMzdk
https://t.me/+4rzL1Wg0GQ0zMzdk
393 views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 20:07:23
አደይ ድራማን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኛሉ ከDSTV በመውሰድ በየቀኑ እየለቀቅን ነው ቻናላችንን ይቀላቀሉት

https://t.me/ALBOTV_12
https://t.me/ALBOTV_12
201 views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 12:27:11
#ብሔራዊ_ፈተና

ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ ቢ ሲ) የሰጡት ቃል ፦

- ፈተና ማተም ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል።

- ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ የሚፈቀዱላቸው ፦

• መጽሐፍት፣
• ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣
• የንጽህና መጠበቂያዎች
• የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦

• ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
• ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣
• ሀብሎች ፣
• የጸጉር ጌጦች
• ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም።

- የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ።

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER
1.3K viewsedited  09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ