Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ትምህርት መስከረም 9 ይጀምራል በ2015 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ | Ministry of education®

በአዲስ አበባ ትምህርት መስከረም 9 ይጀምራል

በ2015 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሆኖ ይሰጣል ተባለ

የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሀገር አቀፍ ሆኖ ይሰጣል።

የ2015 ዓመት መደበኛ የትምህርት ዘመን መስከረም 9 ቀን እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በ2015 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ተናግረዋል።
በአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ላይ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ በ2014 የትምህርት ዘመን ላይ የተከናወነ ሲሆን አዲሱ ስረዓተ ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ በሁሉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ተግበራዊ ይሆናል።

በሌላ በኩል በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም በከፊል በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 የትምህርት ዘመን የሙከራ ትግበራ ከተከናወነ በኃላ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ ይደረገል።

በ2015 ዓመት የትምህርት ዘመን 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፣የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ እንዲሁም 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ የማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል ፡፡በ2015 የትምህርት ዘመን ላይ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲተገበር በተለይ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ እና ከዚህ ቀደም በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረም በጋራ መሰራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የመጽሀፍ ስርጭትን በተመለከተ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በተማሪዎች እጅ እንዲደርስ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ አበበ ቸርነት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER