Get Mystery Box with random crypto!

ክሮም የምትጠቀሙ በአስቸኳይ update አድርጉ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል በክሮም ብሮዉዘሩ | Ministry of education®

ክሮም የምትጠቀሙ በአስቸኳይ update አድርጉ

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል በክሮም ብሮዉዘሩ (chrome browser) ላይ ተጠቃሚዎችን ለከፍተኛ የሳይበር ጥቃት የሚያጋልጥ ክፍተት መገኘቱን ተከትሎ አስቸኳይ የክፍተት መሙያ አቅርቧል።

ኩባንያዉ ለክፍተቱ መሙያ የክሮም እትም #Chrome 103.0.5060.114 ያቀረበ ሲሆን ይህም ለማይክሮሶፍት ዊንዶዉስ ተጠቃሚዎች የሚሆን መሆኑ ጠቁሟል።

ይህ የደህንነት ማዘመኛ በጉግል ኩባንያ የቀረበለት ክፍተት ከዚህ በፊት ያልተለየ እና የመረጃ መንታፊዎች በተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚያስችላቸዉ መሆኑን ጉግል ይፋ አድርጓል።

ይህ ቀደሞ ያልተለየ የሳይበር ጥቃት አጋላጭ ክፍተት #zero_day_vulnerability በክሮም ብሮዉዘር ላይ ሲደርሰ የፈረንጆቹ 2022 ከገባ ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑም ታዉቋል።
በመሆኑም የክሮም ብሮዉዘር ተጠቃሚዎች የክፍተቱን አደገኛነት በመረዳት በአስቸኳይ የመረጃ ማፈላለጊያዉን እንዲያዘምኑ ጉግል መክሯል።

Via: —INSA

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER