Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ መሰጠት ጀምሯል። ፈተናው | Ministry of education®

#AddisAbaba

የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ መሰጠት ጀምሯል።

ፈተናው ከዛሬ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሦሥት ቀናት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ማስታወቁ አይዘነጋም።

ከተማ ዐቀፍ ፈተናው በአዲስ አበባ በሚገኙ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ ሲሆን 1 ሺህ 800 ፈታኞች እና 450 ሱፐር ቫይዘሮች ፈተናውን እየተቆጣጠሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በዛሬው የፈተና ውሎ ጠዋት የአማርኛ እና እንግሊዘኛ ፈተናዎች እየተሰጡ ሲሆን ከሰዓት ሂሳብ እና ባዮሎጂ ፈተናዎች ይሰጣሉ።

በአጠቃላይ በከተማዋ ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER