Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና በ10 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ 31 ማዕከላት ይ | Ministry of education®

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና በ10 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ 31 ማዕከላት ይሰጣል፡፡

ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በክልሉ ሁሉም የመፈተኛ ተቋማት እና ማዕከላት በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ምክትል ኮሚሽነር እንየው ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ወረዳን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቀመጠው ጊዜ ለማድረስ በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ዝግጅት ማድረጉን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ውቤ አጥናፉ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች የወረዳ ትራንስፖርት ቢሮ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሰረት በጊዜ እየተገኙ እንዲስተናገዱ ጠይቀዋል፡፡

ሀገራዊ ግዴታቸውን በአግባቡና በሀላፊነት የማይወጡ የትራንስፖርት ማህበራትና ባለሀብቶች በትራንስፖርት መመሪያ እና በሕግ ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በሚጓጓዙባቸው ቀናት መደበኛ ትራንስፖርት ስለማይኖር ሕዝቡ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንዲተባበር ጥሪ አድርገዋል፡፡ #አሚኮ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER