Get Mystery Box with random crypto!

ለቀጣይ ዙር የ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች; ።።።፡።።።።::::: ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ እየተ | Ministry of education®

ለቀጣይ ዙር የ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች;
።።።፡።።።።:::::
ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ እየተቃረበ መሆኑን አውቃችሁ በተዘጋጃችሁት ልክ ተረጋግታችሁ ለመስራት ጥረት እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በተለይ በግጭት አካባቢ የነበራችሁ ተማሪዎች በብዙ ችግር ውስጥ ሁናችሁ ስትዘጋጁ እንደቆያችሁ ይታወቃል። ችግራችሁን በመገንዘብም ቀጣዩ ዙር ፈተና የተዘጋጀላችሁ መሆኑን በመገንዘብ ዕድላችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት ምክራችንን እንለግሳለን።

በአንደኛው ዙር ፈተና (በተለይ በማህበራዊ ሳይንስ ፈተና) ወቅት የተከሰቱት ችግሮች እናንተንም እንዳይገጥሟችሁ ማስታወስ ተገቢ ነው ብዬ ስላሰብሁ የሚከተሉትን ላጋራችሁ ወደድሁ:

1. በ2013 ተፈትነው ነገር ግን በድጋሚ በመደበኛው ኘሮግራም ለመፈተን እድል የነበራቸው የተወሰኑ ተማሪዎች(ሁሉንም ለማለት አይደለም) ሲያጠኑ ስላልከረሙ እና የተሻለ ውጤት ማምጣት የማይችሉ መሆናቸውን በመገመት የፈተና ስርዓቱን ለማወክ ባደረጉት ሙከራ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው እና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ተስፋ የነበራቸው ተማሪዎቻችን ከፈተና ተስተጓጉለውብናል። ይህ ድድርጊት እጅግ በጣም ስሜታችንን ጎድቶት አልፏል። በመሆኑም በቀጣይ እንዳይደገም ትምህርት መውሰድ ተገቢ ነው።

2. አንዳንድ ተማሪዎች ፈታኞችን ያልተገባ ንግግር በመናገር እና በማበሳጨት እንዲሁም የክፍል ፈተና ስርዓቱ እንዲረበሽ በማድረግ ፈታኞች ፈተናውን በችግር እንዲመዘግቡት የማድረግ ያልተገባ ግፊትም ተስተውሏል።

ይህ ድርጊት ምንጩ አስከአሁን ግልፅ ባይሆንም በተለይ ፈታኞች በሳል ሁነው ችግሩን በጥበብ ማለፍ ካልቻሉ ተፅዕኖው ቀላል እንደማይሆን ስጋት መፍጠሩ አልቀረም።

በጊዜው ሁሉም ቦታ ለመድረስ ባይቻልም መድረስ በቻልንባቸው የፈተና ጣቢያዎች ፈታኞችን ለማረጋጋት እና ድርጊቱ ውስን ቁጥር ያላቸው የተለዬ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው በትዕግስት የፈተና ስርዓቱን እንዲመሩት ለማግባባት ተሞክሯል። ሌሎች ያልደረስንባቸው ጣቢያዎች ሁኔታ ምንይመስል እንደነበር ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ፈታኞች ይህን ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን በትዕግስት እና በጥበብ ተወጥተውት እና ለብዙሀኑ ተማሪዎች ሲባል የአንዳንድ ተማሪዎችን ያልተገባ ስነምግባር በትዕግስት አልፈውት እንደሚሆን እንጠብቃለን።

3. በተለይ ድብረታቦር ዩኒበርስቲ ላይ የተፈጠረው ያለመረጋጋት ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲፈተኑ የሚያስችል ሁኔታ ነበር ብሎ ለማለት ያስቸግራል። የነበረው ሁኔታ ፈተና አቋርጠው በሄዱት ላይ ብቻም ሳይሆን በፈተና ሂደቱ ውስጥ በነበሩት ተማሪዎች ላይም ተፅዕኖው ከባድ እንደሚሆን ይገመታል።

በዚህም ሁከት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ውጤታማ ተማሪዎቻችን ባላሰቡት መንገድ ተስተጓጉለውብናል።

በአጠቃላይ የመጀመሪያው ዙር ፈተና እንደሀገር የመጀመሪያ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ከትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ ከት/ቢሮውም በኩል የነበሩ ከቅድመዝግጅት መጓደለም ጋር የተያያዙት መለስተኛ ችግሮች (በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ወቅት ማስተካከያ የተደረገባቸው ችግሮች)ተጨምረውበት በርካታ ተማሪዎቻችን ከፈተና ስርዓቱ የተስተጓጎሉበት ሁኔታ መፈጠሩ የትምህርት ማህበረሰቡን እጅግ በጣም ያሳዘነ ክስተት ሆኗል።

የነበሩ የቅድመዝግጅት መጓደሎችን እና አጠቃላይ ሂደቱን በሚመለከት ለሚመለከተው አካል በጊዜው የግምገማ ሪፓርት ስላቀረብን እዚህ ላይ መዘርዘሩ አያስፈልግም።

በአጠቃላይ ከግምገማ ሪፓርታችንም ሆነ ከሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት ውሳኔ ሰጭው አካል የሚሰጠው ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣዩ ዙር ፈተና የባለፋት ችግሮች በድጋሜ እናንተንም እንዳያጋጥሟችሁ ተገቢውን የጥንቃቄ ቅድመዝግጅት እንድታደርጉ ከወዲሁ እያሳሰብሁ መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!
ማተብ ታፈረ(ዶ/ር)

የአብክመ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER