Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚንስቴር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዲጂታል ለመስጠት ታብሌቶችን አገር ውስጥ ለማስመ | Ministry of education®

ትምህርት ሚንስቴር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዲጂታል ለመስጠት ታብሌቶችን አገር ውስጥ ለማስመረት እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ ማለቱን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሚንስቴሩ የመስሪያ ቤታቸውን የሥራ አፈጻጸም አስመልክተው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ፈተናውን በኢንተርኔት ለመስጠት በውጭ አገር የቴክኖሎጂ ባለሙያ ኢትዮጵያዊያን የሶፍትዌር ሥራዎችን እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑን ሚንስትር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል ተብሏል። ሚንስቴሩ ታብሌቶቹን አገር ውስጥ ለማሰራት የወሰነው፣ ታብሌቶቹን በውጭ ለመግዛት ዋጋቸው በመወደዱ እንደሆነ መግለጹን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER