Get Mystery Box with random crypto!

የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሥራ ማቆም አድማን ማን ጠራው? በዩኒቨርሲቲዎች መምህራን የፊታችን ሰኞ ኅ | Ministry of education®

የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሥራ ማቆም አድማን ማን ጠራው?

በዩኒቨርሲቲዎች መምህራን የፊታችን ሰኞ ኅዳር 26 ቀን፣ ይደረጋል የተባለውን የሥራ ማቆም አድማ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች መምህራን እና ቴክኒክ ረዳቶች ማኅበር እንዳልጠራው አስታወቀ።

የኢትዮጵያ 42 ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አለማቅረቡን ፕሬዝዳንቱ ዶክተር በፍቃዱ ዘለቀ ዛሬ ለDW ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር በፍቃዱ እርሳቸው በሚመሩት ማኅበር ስም ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረቡት አስራ አራት ጥያቄዎች በእርግጥም ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች መሆናቸውን ለዶይቼ ቬለ ቢያረጋግጡም የሥራ ማቆም አድማ ግን እንዳልተጠራ ገልጸዋል። ማኅበሩ ይህንን ያደረጉት የማናውቃቸው የተደራጁ አካላት ናቸው ብሏል። ይህን ያደረጉ ያላቸውንም እንደሚከስ አሳውቋል።

በተቃራኒው ዶይቸ ቬሌ ያነጋገራቸው የዩኒቨርስቲ መምህራን የሥራ ማቆሙን አድማ ለማድረግ እንደውም ዘግይተናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበርን ስም እና ዓርማ በያዘ ደብዳቤ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ኅዳር 15 ቀን፣ 2014 ዓ.ም የተሰራጨው መግለጫ አስራ አራት ጥያቄዎችን የያዘ ነው። ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል የደመወዝ ጭማሪ፣ የደረጃ ዕድገት፣ የቤት አበልን የተመለከቱ ይገኙበታል። ደብዳቤው በተጨማሪ ሥራዎች የሚገኝ ገቢ ላይ የግብር ቅነሳ፣ የሦስተኛ ዲግሪ የምርምር ገንዘብ መጠን፣ የመምህራን የዝውውር ጉዳዮችን ጭምር ያካተተ ነው።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER