Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለ | Ministry of education®

#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ?

- "የፈተና ዝግጅት እና ህትመት" ከቀድሞው እንዲለይ በኮድ ብዛት እና በገፅ አወቃቀር በመለየት በሁለቱም የትምህርት መስኮች " 12 ኮድ " እንዲኖር እና የመለያ ኮዱ ከሚታወቅበት 2 ኮድ ወደ 3 ተቀይሮ ፈተናው ተሰጥቷል።

- #ስልክ እና ማንኛውም #ኤሌክትሮኒክ_መሳሪዎችን ተፈታኞች ይዘው እንዳይመጡ መልዕክት ቢተላለፍም በ33 የፈተና ጣቢያዎች 59 ተፈታኞች #ስልክ_ይዘው ገብተው ለመጠቀም ሙከራ አድርገው ተይዘዋል።
ጫት፣
አደንዛዥ ዕፅ፣
ሲጋራ፣
ስለታማ ነገሮች፣
ጥይት፣
አልኮል ..... ወዘተ ተፈታኞች ይዘው በመምጣት በተለያየ መልክ ለማስገባትና በአንዳንድ ቦታዎችም ለመጠቀም ሙከራ አድርገዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ " ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ግቢ " የሚወስደው ድልድይ በመደርመሱ ምክንያት 451 ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል ፤ 1 ተማሪ ህይወቱ ሲያልፍ 232 ተማሪዎች ቀላል የአካል ጉዳት ፣ 201 ተማሪዎች መካከለኛ ጉዳት ፣ 13 ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ፣ 5 ተማሪዎች በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ 5 የፀጥታ ኃይሎች እና 2 ፈተና አስፈፃሚዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- " በሶስት ዩኒቨርሲቲዎች " ቀደም ሲል በነበር የጤና እክል ምክንያት 3 ተማሪዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ በጉዞ ወቅት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ የተወሰኑ ተማሪዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ፈተና መውሰድ ያልቻሉና በከፊል የተፈተኑ በአንድ ወር ጊዜ የሚዘጋጀውን ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል። ተፈታኞቹ የጤና ሁኔታቸው ለፈተናው የማያበቃቸው ካሉ ከ2015 ዓ/ም ተፈታኞች ጋር በመደበኛነት እንዳፈተኑ ይደረጋል።

- " ፈተና አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ዳግም በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እንድል አይሰጣቸውም፤ በግል በ2015 ዓ.ም የመፈተን መብታቸው የተጠበቀ ነው።

በ " ማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ፈተና ሳይፈተኑ የወጡ ተማሪዎች ፦

ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ (1,700 ተማሪዎች)
ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (1,226 ተማሪዎች)
ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (2,711 ተማሪዎች)
ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (7,356 ተማሪዎች) በድምሩ 12,993 ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተና ሳይጀምሩና የአንድ ቀን ሁለት ፈተና ከወሰዱ እንዲሁም የሁለት ቀን 4 ፈተናዎች ከወሰዱ በኃላ " አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች ከዚህ በኃላ በ " መደበኛ ተማሪነት " መፈተን #የማይችሉ ሲሆን በ2015 በግል መፈተን ይችላሉ።

- በታወቁ የጤናና ሌሎችም እክሎች ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈተናሉ።

- " የፈተናው ዉጤት " በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈተኑ ተማሪዎች በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሰረት ከተፈተኑ በኋላ የሁለቱንም ዉጤት ተጠቃሎ ይፋ ይደረጋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER