Get Mystery Box with random crypto!

' ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ይገለጻል።' የትምህር | Ministry of education®

" ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ይገለጻል።"

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)


የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ወይም 98 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ያልወሰዱና በተለያዩ አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ እንዲሁም በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

በአራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ12 ሺህ በላይ ፈተናውን አንፈተንም ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ #እንደማይችሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ነገር ግን #በግል መፈተን ይችላሉ ብለዋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንደሚገለጽ ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER