Get Mystery Box with random crypto!

በፊሊፒንስ የሚገኝ ኮሌጅ ተማሪዎች ፈተና እንዳይኮራረጁ “ጭንቅላታችሁን ሸፍኑ” ማለቱ እያነጋገረ ነ | Ministry of education®

በፊሊፒንስ የሚገኝ ኮሌጅ ተማሪዎች ፈተና እንዳይኮራረጁ “ጭንቅላታችሁን ሸፍኑ” ማለቱ እያነጋገረ ነው

በፊሊፒንሷ ልጋዝፒ ከተማ የሚገኝ አንድ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኝ ኮሌጅ ተመሪዎች ወደጎናቸው አጮልቀዉ በመመልከት ፈተና እንዳይሰርቁ በማሰብ ጭንቅላታቸውን የሚሸፍን ነገር እንዲለብሱ ታዘዋል።

ይህንን ተከትሎም ተማሪዎች ካርቶኖችን፣ የእንቁላል መደርደሪያዎችን፣ የሞተር ሳይክል ሄልሜት እንዲሁም ከሌሎች የወዳደቁ ነገሮች በራሳቸው ፈጠራ የሰሯቸውን መሸፈኛዎች ለብሰው በፈተናው ላይ መገኘታውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በባይኮል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ ማንዳን፤ ተማሪዎች እንዳይኮራረጁ የተተገበረው አሰራር ውጤታማ እንደነበረ አስታውቀዋል።
በፈተና ወቅት ፊት መሸፈን እንዲተገበር ያነሳሳቸው ከዓመታት በፊት በታይላንድ ውስጥ ተተግብሮ ያዩት አንደሆነም ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ ተናግረዋል።
በፈረንጆጁ 2013 ላይ የባንኮክ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፈተና ላይ በሚቀመጡበት ወቅት በግራና በቀኝ በኩል ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ በወረቀት እንዲሸፍኑ በማድረግ ፈተና እንዲፈተኑ ተደርጎ ነበር።

ከዚህ በመነሳት “የፀረ ኩረጃ ኮፍያ” በባይኮል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ መተግበሩንም ፕሮፌሰሯ አስታውቀዋል።
ፕሮፌሰር ሜሪ ጆይ፤ ጥብቅ የፈተና ቁጥጥር ተማሪዎች ለማጥናት አነሳስቷል ያሉ ሲሆን፤ ይህም የተሸለ አፈጻጸም ማስገኘቱንም ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት በርካቶች ፈተናቸውን በአግባቡ እና በተሰጣቸው ጊዜ ማጠናቀቃቸውን የገለጹት ፕሮፌሰሯ፤ ፈተና ሲሰርቅ የተያዘ ተማሪ እንደሌለም አስታውቀዋል።

#አልዓይን

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER