Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopia — TIKVAH-ETHIOPIA
ርዕሶች ከሰርጥ:
Gbe
Questionandanswer
Globalbankethiopia
Bankinethiopia
Oursharedsuccess
Furtheraheadtogether
Mpesasafaricom
Addisababa
Update
Genocide
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopia
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.34M
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 430

2021-09-30 16:27:37
#Update

አዲሱ የአፋር ክልል ም/ቤት አቶ አወል አርባን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ።

አዲሱ የአፋር የክልል ም/ቤት አቶ አወል አርባን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሾሟል።

አቶ አወል አርባ የክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡

Credit : የአፋር ክልል ማስ ሚዲያ

@tikvahethiopia
179.3K viewsedited  13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 16:25:34
#Update

አቶ አወል አርባ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዲሆኑ በእጩነት ቀርበዋል።

Photo Credit : አፋር ማስ ሚዲያ

@tikvahethiopia
169.6K viewsedited  13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 16:20:32
#Update

የአፋር ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ አሲያ ከማልን ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል። ወ/ሮ መየረም መሀመድ አሓው ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
157.5K viewsedited  13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 21:53:29
95.8K viewsedited  18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 21:48:37
#ማስጠንቀቂያ

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ሲያበር የተገኘ በሕግ እንደሚጠየቅ አስጠንቅቋል።

ለዜጎች ሰላም መረጋገጥ እንዲሁም የቁልፍ መሰረት ልማቶችን ደህንነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመጠበቅና ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ድሮኖችን ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ ለቀረፃ መጠቀምም ሆነ ማብረር እንደማይቻል መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ለቀረፃ ሲጠቀሙ እና ሲያበሩ እየተስተዋለ መሆኑን የገለፀው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጉዳዩ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ በጥብቅ አስጠንቅቋል።

ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀምና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ በህግ ይጠየቃልም ብሏል።

Credit : የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት

@tikvahethiopia
92.6K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 21:47:24
#ETHIOPIA

ሀገራችን ኢትዮጵያ ተጨማሪ 46 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 46 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,750 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,218 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 806 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ #TikvahFamily

@tikvahethiopia
87.5K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 19:54:02
142.2K viewsedited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 19:52:06
#Diredawa : ድሬዳዋ ከተማ ዛሬ አዲስ መንግስት መስርታለች።

ዛሬ ከሰዓት በተካሃደው የድሬዳዋ ከተማ አዲስ መንግስት መስረታ የከተማው ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሃርን በሙሉ ድምፅ ከንቲባ አድርጎ ሲሾም በከንቲባው የቀረቡትን የካቤኔ አባላትንም ሹመት አፅድቋል።

ሹመታቸው በምክር ቤት የፀደቀላቸው የካቢኔ አባላት የሚከተሉት ናቸው ፦

1. ም/ከንቲባና ንግድ ቢሮ - ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ
2. የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ/ የመንግስት ተጠሪ - ኢብራሂም ዩሱፍ
3. ፋይናንስ ቢሮ - ሱልጣን አሊይ
4. ቴክኒክና ሙያ ቢሮ - ሮቤል ጌታቸው
5. ግብርና ቢሮ - ኑረዲን አብደላ
6. ኮንስትራክሽን - ኢ/ር ጀማል ኢብራሂም
7. ጤና ጥበቃ ቢሮ - ለምለም በዛብህ
8. ፍትህ ቢሮ - አብዱሰላም አህመድ
9. መሬት ልማት ቢሮ - ሳጂድ አሊይ ሁሴን
10. ትምህርት ቢሮ - ሙሉካ መሀመድ ሁሴን
11. መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ - ኢስቂያስ ታፈሰ
12. ሴቶችና ህጻናት - ፈጡም ሙስጠፋ ሀቢብ
13. ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ - አቡበከር አዶሽ ኦልሀዬ
14. ዋናው ኦዲተር - ጫልቱ ሁሴን
15. ብዙሃን መገናኛ - አብዱሰላም መይደኔ

Credit : ድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
132.6K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 18:14:18
" ስራ ዝግ ሆኖ ይውላል "

ነገ መስከረም 20 የሚካሄደው ምርጫን እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ ስራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

ስራ ዝግ ሆኖ የሚውለው ፦
- በሐረሪ ክልል፣
- በሶማሌ ክልል፣
- በደ/ብ/ብ/ህ ክልል ፦
• በምእራብ ኦሞ ዞን፣
• በደቡብ ኦሞ ዞን፣
• በቤንች ሸኮ ዞን፣
• በሸካ ዞን፣
• በጌዲዮ ዞን፣
• በሃድያ ዞን፣
• በጉራጌ ዞን፣
• በጋሞ ዞን፣
• በካፋ ዞን፣
• በወላይታ ዞን ፣
• በዳውሮ ዞን፣
• በባስኬቶ ልዩ ወረዳ እና በኮንታ ልዩ ወረዳ ነው።

ምርጫ ቦርድ ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች እና ዞኖች የሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ስራ ዝግ እንዲያደርጉ አሳውቋል።

ቦርዱ ፥ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የእለት ተእለት አገልግሎት ሰጪዎች (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወዘተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን እንደሚችሉ ገልጾ እነዚህ ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አይጠበቅባቸውም ብሏል።

የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም በተጠቀሱት ክልሎች እና ዞኖች ዜጎች ድምጽ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና እቅዶችን እንዳይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምጽ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉም ቦርዱ አበረታቷል።

@tikvahethiopia
166.9K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 16:40:18
173.7K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ