Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopia — TIKVAH-ETHIOPIA
ርዕሶች ከሰርጥ:
Furtheraheadtogether
Mpesasafaricom
Addisababa
Genocide
Rwanda
Remembering
Kwibuka
Safaricomethiopia
Nevacomputer
Tikvahethiopiafamilyhawassa
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopia
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35M
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 432

2021-10-01 21:02:31
122.0K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 21:01:58
#ETHIOPIA

ሀገራችን ኢትዮጵያ ተጨማሪ 48 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 48 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 10,752 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,410 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 802 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ #TikvahFamily

@tikvahethiopia
112.4K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 20:18:20
137.7K viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 19:26:43
154.3K viewsedited  16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 17:03:03
#ATTENTION

" የበረሃ አንበጣ መንጋን ለመከላከል በቂ ቅድመ ዝግጅት ሊደረግ ይገባል " - የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የበረሃ አንበጣ መንጋን ለመከላከል በቂ ቅድመ ዝግጅት ሊደረግ ይገባል ሲል ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ አሊ ሰይድ እንደተናገሩት በአፋር ክልል የተከሰተው የበረሃ አንበጣ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በመስፋፋቱ ዞኑ አጎራባች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ ስጋትን ፈጥሯል፡፡

መንጋው በአፋር ክልል የሚመገበውን እፅዋት እያገባደደ በመሆኑና አዛኛውም መብረር ወደሚችልበት ደረጃ የተሸጋገረ ስለሆነ አጎራባች የሆኑ የዞኑ ወረዳዎች ፦
- ወረባቦ
- ቃሉ፣
- ተሁለደሬ፣
- አምባሰል፣
- አርጎባ እና በሌሎችም ወረዳዎች የሚገኙ አርሦአደሮች ፣የአንበጣ መከላከል ግብረ ሀይል እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አቅም በፈቀደ መንገድ ሁሉ ለመከላከል በቂ ዝግጅት ሊያደርጉ እንደሚገባም ነው አቶ አሊ ያሳሰቡት፡፡

የበረሃ አንበጣው ከአፋር ክልል ውጭ አጎራባች ከሆኑ አገራትም ሊመጣ ስለሚችል ስጋቱ ከደቡብ ወሎ ዞንም አልፎ ለሌሎችም አካባቢዎች ሊሆን እንደሚችልም ነው አቶ አሊ የጠቆሙት፡፡

ባለፈው ዓመት የደረሰው የሰብል እና የእንስሳት መኖ ውድመት እንዳይደገም መንጋውን ለመከላከል የበላይ አካላትን ድጋፍ መምሪያው መጠየቁን የገለፁት አቶ አሊ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ካልሆነም ደግሞ ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ መዋቅሮችና አደረጃጀቶች ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

መረጃው የደረሰን ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
176.5K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 17:01:36
#Tigray : የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙት ባልደረቦቹ የመጠጥ ውሃ ማጣሪያዎችን በመጠገን ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

በትግራይ ክልል ሽራሮ የሚገኙ ከ30,000 በላይ የሚሆኑ በግጭቱ የተጎዱ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ተፈናቃይ ሰዎች የመጠጥ ውሃ ማግኘታቸውን መቀጠላቸውንም አመልክቷል።

@tikvahethiopia
158.7K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 16:59:59
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የተሾሙትን ፦
- የታይላንድ ፣
- የኒውዝላንድ ፣
- የዴንማርክ ፣
- የጅቡቲ ፣
- የአውስትራሊያ ፣
- የየአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የግብፅ አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ የኢትዮጵያን ወቅታዊ እና ተጨባጭ ሁኔታ ለአምባሳደሮቹ እንዳብራሩላቸው የተገለፀ ሲሆን ፤ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረትም ሆነ ከየሀገራቱ ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አጽንኦት ሰጥተዋል።

Credit : Office of the President,Ethiopia

@tikvahethiopia
155.6K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 16:30:46
በአማራ ክልል የተፈናቃዮች ቁጥር አሻቀበ።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 789 ሺህ መድረሱን ገለፀ።

ተቋሙ ይህን የገለፀው ለአል ዐይን አማርኛ በሰጠው ቃል ነው።

ህወሓት በአማራ ክልል አምስት ዞኖች ፦
- በሰሜን ወሎ፣
- በዋግ ኸምራ፣
- በደቡብ ጎንደር፣
- ሰሜን ጎንደር እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ጥቃት ከፍቶ በርካታ ንጹሀንን አፈናቅሏል ሲል ተቋሙ አሳውቋል።

በአጠቃላይ በአማራ ክልል 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ተፈናቃይ ዜጎች በመጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 789 ሺህ ያህሉ ህወሓት በከፈተው ጦርነት የተፈናቀሉ መሆናቸውን የክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም አስረድቷል።

ቀሪዎቹ ተፈናቃዮች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ ከኦሮሚያ ፣ ከትግራይ ፣ ከአፋር፣ ከጅቡቲ እና በክልሉ ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች የተፈናቀሉ መሆናቸውን ገልጿል።

Credit : አል ዓይን
Photo : ደሴ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
157.8K viewsedited  13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 16:29:34
ፎቶ : የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክብረ በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በፍፁም ሰላም ተከብሯል።

በክብረ በዓሉ ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ የሃይማኖት አባቶች እና የሃይማኖቱ ተከታዮች ተገኝተው ነበር።

በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር የፀጥታ ኃይሎች ሰፊ ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበር መገለፁ አይዘነጋም።

Photo Credit : AMC

@tikvahethiopia
148.6K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 16:29:10
Maryland International College, fully-accredited by Ethiopian Higher Education Relevance and Quality Agency (HERQA) in its TWO WELL-DESIGNED CAMPUSES, is registering Masters Degree students with discounts available only for first comers (MA applicants).
- There will be free Project Management Software trainings

Masters Degree Late Registration Deadline: Until October 12/2021.

For more info: 0940102029/0935656939
Campus Locations: 1. Hayahulet (Next to Capital Hotel) and 2. Global Campus (Next to Global Hotel on your way to Stadum)
Website: www.marylandic.com
162.0K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ