Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopia — TIKVAH-ETHIOPIA
ርዕሶች ከሰርጥ:
Gbe
Questionandanswer
Globalbankethiopia
Bankinethiopia
Oursharedsuccess
Furtheraheadtogether
Mpesasafaricom
Addisababa
Update
Genocide
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopia
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.34M
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-28 20:03:07
" ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " - ሞህሰን አል-ማንዳላዊ

የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ።

እንዲሁም፦

- ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

- ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ

- ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች

- ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል።

" በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ፎቶ፦ ፋይል

#Iraq

@tikvahethiopia
209.1K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 18:55:24
#Ethiopia

" የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53% ድርሻ ይዟል " - የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት " ለሁለተኛ ጊዜ በጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ እንዲሆን እያደረገው " ነው ሲል ገለጸ።

የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53% ድርሻ ይዘዋልም ብሏል።

ማህበሩ ምን አለ ?

- በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ ይዘዋል።

- እነዚህ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸው በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው። እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

- የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ የቦንዳ ልብሶች ተሞልተዋል።

- የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር በተለያዩ መንገዶች የሚገቡ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋ እና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በ ' ኢትዮጵያ አየር መንገድ ' በኩልም በተለያዩ ሁኔታዎች ይገባሉ።

- ሀገሪቱ በአማካኝ 54 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የጨርቃጨርቅ አልባሳት ያለ ክፍያ (በዜሮ ወጪ) ድንበር አቋርጠው ይገባሉ። በዚህም ኢትዮጵያ በዓመት ከታክስ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ይደርስባታል።

- በህገወጥ መንገድ የሚገቡ ልብሶች የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪውን መፈታተናቸውን ቀጥለዋል ፤ ለኪሳራ እንዲዳረጉም እያደረጉት በመሆኑ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ቅሬታዎችን ያቀረብን ቢሆንም ምላሽ አላገኘንም።

ምንጭ ፦ የካፒታል ጋዜጣ

@tikvahethiopia
225.8K viewsedited  15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 17:12:02
#ኢራቅ

የኢራቅ ፓርላማ #ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ።

በአዲሱ ሕግ ፦

የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤

ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤

" ሆን ብለው " እንደ #ሴት የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የሕጉ ዓለማ ፥ " የኢራቅን ማህበረሰብ ከሞራል ዝቅጠትና ግብረ ሰዶማዊነት ከሚያደርሰው አደጋ ለመጠበቅ ነው " ተብሏል።

ረቂቁ መጀመሪያ ላይ ግብረሰዶማውያን #በሞት እንዲቀጡ የሚል የነበረው ቢሆንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ መሻሻሉ ነው የተሰማው።

የኢራቅ ፓርላማ አባል የሆኑት አሚር አል-ማሙሪ ፥ " አዲሱ ሕግ #ኢስላማዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚቃረኑ ልዩ ጉዳዮችን ለመዋጋት ትልቅ እርምጃ ነው " ብለዋል።

#አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መ/ ቤቷ በኩል ሕጉን ፤ " ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ጠንቅ ነው " በማለት ሕጉን ተቃውማለች።

" ሕጉ የኢራቅን ኢኮኖሚ የሚያቀዛቅዝ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ያዳክማል" ብላለች።

የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሕጉን ተቃውመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጮች #ቢቢሲ እና #ሮይተርስ መሆናቸውን ይገልጸል።

@tikvahethiopia
227.3K viewsedited  14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 17:11:28
#FakeNews

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም።

ከወራት በፊት መሰል የፈጠራና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ የ #የሶማሊያ አክቲቪስቶችና የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከሰሞኑን ዳግም የፈጠራ ወሬዎችን ፅፈው ማሰራጨትን ይዘዋል።

እያሰራጩ ካሉት ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ አንዱ " በአዲስ አበባ የተለየ ሁኔታ እንዳለ ፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደጨመረ፣ በየቦታው ወታደሮች እንደተበተኑ " የሚገልጽ ነው።

ይህ ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ ሲሆን በከተማዋ ውስጥ አንዳችም የተለየ የወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም።

ምንም እንኳን ጉዳዩ ውሸት ቢሆንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህ ሀሰተኛ መረጃ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ፣ እያጋሩት እንደሆነ መመልከት ተችሏል ስለሆነም ጥንቃቄ አድርጉ።

#AddisAbaba #Ethiopia

@tikvahethiopia
190.7K views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 17:11:20
#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው

በቀን በ12 ብር በወር በ350 ብር ብቻ !

ተወዳጁን ሀገርኛ ድራማዎችን እና መዝናኛዎችን የምናገኝበት አቦል ቲቪ ከሜዳ ወደ ጎጆ ፓኬጅ መጣ!

ምን ይሄ ብቻ ኒክ ጁኒየር በአማርኛ፥ ዚ-ዓለም የተከታታይ ድራማ ቻናል እና ሌሎችም የዲኤስቲቪ ቻናሎችን በጎጆ ፓኬጅ ያገኛሉ።

አሁን ጎጇችን ሞላ፤ በወር 350... በቀን 12ብር ብቻ

#DStvEthiopia #AbolTV #NickJrAmh #TraceMuzika #Zeeዓለም
190.6K views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 12:10:58
" ሆሣዕና '' (የዐብይ ጾም 8ኛ ሳምንት)

ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣዔ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም  " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው።

ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች እና ሕፃናት '' ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም '' በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት ነው፡፡ 

ይህ ዕለት በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘንባባ ተይዞ፣ እየተዘመረ እጅግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ይታሰባል።

በዐብይ ጾም ከሰርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሣዔ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡

በዚህ ጊዜ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ካህናት መስቀል በእጃቸው አይዙም፣ አያሳልሙም ፣ ይፍቱኝ ተብሎ ወደካህን አይቀረብም፤ ይህ ሳምንት የጌታን የመጨረሻው ስቃይ የሚታሰብበት ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
218.1K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 22:51:00
" ... ትጥቅ ሙሉ በሙሉ የማስፈታት ሁኔታ የሚፈጠረው ለትግራይ ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው " - አቶ ኢያሱ ተስፋይ

ከቀናት በፊት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፥ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከመከረ በኃላ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

በመግለጫው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ብዙ ውጤቶች እና እፎይታን ያስገኘ ቢሆንም አሁንም ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር።

ከነዚህ ቀሪ ስራዎች አንዱ የ ' ህወሓት ' ትጥቅ መፍታት እንደሆነ ጠቁሞ ፤ " በሰላም ስምምነቱ መሰረት ህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ፤ በብሄራዉ ተሃድሶ ኮሚሽን እቅድ መሰረት በፍጥነት መተግበር አለበት " ብሎ ነበር።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው ህወሓት በስምምነቱ መሰረት " ከኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ / የፌዴራል ጸጥታ ኃይል ውጭ ያሉ ማንኛውም ኃይሎች ከትግራይ የአስተዳደር ወሰን እንዲወጡ መደረግ አለበት " ብሏል።

የህወሓት የፕሮፖጋንዳ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኢያሱ ተስፋይ ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ " ' ለዘላቂ ሰላም ትጥቅ መፍታት አለባቸው የሚለው ችግር የለውም ትክክል ነው " ያሉ ሲሆን " እንደ ትግራይ ህዝብ ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻችን ከተመለሱልን ወደ ልማትና ወደ ዴሞክራሲ ግንባታ ስራችን መሸጋገር እንፈልጋለን " ብለዋል።

" ለሰላም ከማንም በላይ ጥብቅና እንቆማለን ስትራቴጃካዊ ፍላጎታችንም ነው ግን ደግሞ ያ ሰላም ከጥያቄዎቻችን መመለስ ጋር በቀጥታ መያያዝ አለበት እንጂ ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ መብታችን ሳይከበር ዝም ብሎ ሰላም የሚመጣ ነገር አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ለሰላም ብለን ቀደም ብለን ትጥቅ ማስፈታት ጀምረናል። የከባድ ማሳሪያም ርክክብም ከአመት በፊት አድርገናል፣ ከዛ አልፎ ከነበረን ሰራዊት በርካታውን demobilize አድርገናል ፤  " ሲሉ አክለዋል።

" ትጥቅ #ሙሉ_በሙሉ_የማስፈታት_ሁኔታ የሚፈጠረው ለትግራይ ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው። ከፌዴራል ኃይል ውጭ ያሉ የተለያዩ ታጣቂ ኃይሎች በምዕራብ ትግራይ አሉ ህዝባችንን ለብዙ መከራ እየዳረጉ ያሉ በጸለምትም ፣ በደቡብ ትግራይም ስለዚህ አሁን ፌዴራል በጀመረው ነገር እነዚህን ኃይሎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱና ወደ ሌላ ስራቸው እንዲሄዱ የማድረግ ኃላፊነት አለበት " ብለዋል።

ለDDR የሚያስፈልገው ሁሉ በጀትም መመደብ አለበት ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
85.9K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 21:54:51
“... ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም ” - አቶ ንጋቱ ማሞ

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፥ በከተማው በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር ዘንድሮ መጨመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነተ ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ምን አሉ ?

- “ ከተማው ውስጥ ብዙ የግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ። በተለይ አሁን ሕይወታቸውን እያጡ ያሉት በኮንክትራክሽን / በግንባታ ዘርፉ ያሉ የቀን ሠራተኞች ናቸው። ”

- “ የቀን ሠራተኞች በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ብዙ ጊዜ ጉልበታቸውን ነው ይዘው የሚገቡት፤ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ቴክኒካል እውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የላቸውም።  እንዴት የሥራ ላይ አደጋን መከላከል እንደሚችሉ ስለጠና እንኳ አይሰጥም። ”

- “ ' #የቀን_ሠራተኞች_እንፈልጋለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችን የኮንስትራክሽን ሳይቶች ላይ እናያለን። በዚያው ሥራ ያጣ መንገደኛ ይገባል ግን ሥራውን ለመከናውን ምን ሊያጋጥም ይችላል ? ብሎ አስቀድሞ የመገመት እውቀት አይኖርም። ”

- “ ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች ላይ ትልቁ ኃላፊነት ይወድቃል። እነርሱ ደግሞ በሚፈለገው ደረጃ ለዘርፉ ትኩረት እየሰጡ አይደለም። አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም። ”

- “ ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ግንባታው እስኪጠናቀቅ የደህንነት መርሆዎችን ያለመከተል ሁኔታ አለ። ”

Q. መፍትሄውን ምንድነው ?

- “ መፍትሄውማ ፈቃድ ሰጪው አካልም ፈቃድ ከሰጠ በኋላ በየጊዜው ጠብቅ ቁጥጥር በማድረግ ለአደጋ የተጋለጡ አሰራሮችን እየለዩ በህንጻ አዋጁ መሠረት እርምጃዎችን ቶሎ ቶሎ መውሰድ ያስፈልጋል። ”

ሰሞኑን የ7 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የድንጋይ እና አፈር ናዳ አደጋ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ ባሉ ሠራተኞች ላይ ባለመድረሱ ለየት ያለ ቢሆንም ይህንኑ አደጋ ጨምሮ በ2016 ዓ/ም እስካሁን 12 ሰዎች በተለያዩ ጊዜዎችና አደጋዎች ሞተዋል።

የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ጨምሯል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@thikvahethiopia
114.1K views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 21:38:58
“ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ ” - የ9 ዓመቷ ታዳጊ እናት

ልጃቸው ለየልብ ህመም የታመመችባቸው እናት ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲያግዟቸው ተማጽኑ።

ወ/ሮ መባ አላምረው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ሊያ የ3ኛ ክፍል ተማሪ 2ኛ ልጄ ናት። #ልቧ 15 ሚሊ ሜትር #ክፍተት አለው ” ብለዋል።

የልብ ስፔሻሊቲ ዶክተርም፣ “ ‘ችግሩ ክፍተት መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን የቀኝ ልቧ አቅጣጫውን በመሳት ወደ ሳምባዋ ክፍል ደም እየረጨ ነው። ሳምባዋም ወደ ማበስበስ ደረጃ እየደረሰ ነው። በአስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት’ ” እንዳሏቸው አስረድተዋል።

“ በፊት ላይ ‘#የሳንባ #ምች ነው’ እየተባለ ነበር። አሁን ‘የልብ ክፍተት ነው’ ተባለች። #እጇንም #እግሯንም #መሸምቀቅ ጀመራት። ትምህርቷን አቋርጣ ቤት ከተቀመጠች 1 ወር ሆናት ” ብለዋል።

“ ‘ሳንባዋ ለንቅለ ተከላ የሚደርስ ነው’ አሉኝ ” ያሉት እኝሁ እናት፣ ለሰርጀሪው ብቻ 595 ሺሕ ብር፣ የሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ 700 ሺሕ ብር ለቀዶ ጥገና እንደተጠየቁ አስረድተዋል።

የታዳጊዋ እናት፣ “ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ። ሁሉም ያቅሙን በገንዘብም በጸሎትም እንዲተባበረኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳኝ እለምናለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል። 

እናት መባ አላምረውን በስልክ ለማግኘት በ +251939665539 መደወል ይቻላል። የባንክ የሒሳብ ቁጥራቸው 1000470071536 ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
115.9K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 21:12:30
" የፀጥታ አካላት ነን ፤ #በወንጀል_ትፈለጋለህ " በማለት አስፈራርተው ከኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ ገንዘብ የተቀበሉ ግለሰቦች በእስራትና ገንዘብ መቀጣታቸው ተነገረ።

የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾች ፦
1ኛ. ጫላ መገርሳ፣
2ኛ. ለሊሳ በቀለ፣
3ኛ  ዳዊት ጉደታ፣
4ኛ. ዮሃንስ ደረጄ
5ኛ  ብርቱካን ለታ ናቸው።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በመጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በሸገር ከተማ ገፈርሳ ክ/ ከተማ አካባቢ በሚገኝ የኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ የሆነን የግል ተበዳይን " የፀጥታ አካላት ነን ፣ በወንጀል ትፈለጋለህ " በማለት መንገድ ላይ ያስቆሟቸዋል።

በኃላም ከውጭ ወደ ውስጥ እንዳይታይ አድርገው በስቲከር ሸፍነው ወደአዘጋጁት የቤት መኪና ውስጥ በማስገባት ወደ መልካ ናኖ ክ/ከ አንፎ ወደ ተባለ አካባቢ ይወስዷቸዋል።

ከዚህም በኋላ የሞተ ሰው ፎቶ ለግል ተበዳዩ በማሳየትና በመሳሪያ በማስፈራራት ግማሽ ሚሊየን ብር እንዲያመጣና እንደሚለቁት ይገልጻሉ።

ገንዘቡን ካልከፈለ ደግሞ " ወደ ጦር ኃይሎች እንወስድኃለን " በማለት ገንዘብ እንዲከፍል ያስፈራሩታል።

ይህን ተከትሎ የግል ተበዳዩ በባንክ ሂሳቡ ውስጥ 100 ሺህ እንዳለው ይገልጽላቸዋል።

በዚህም ጊዜ 1ኛ ተከሳሽ ባለቤቱ በሆነችው በ5ኛ ተከሳሽ የባንክ ሂሳብ በሞባይል ባንኪንግ የግል ተበዳዩ 100 ሺህ ብር እንዲያዘዋውር ያደረገና ቀሪውን 400 ሺህ ብር እንዲያመጣ በማስጠንቀቅ ይለቁታል።

በህገወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ደግሞ 5ኛ ተከሳሽ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ምንጩን ለመደበቅ በማሰብ በተለያዩ መጠኖች ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅም እንዳዋሉት የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ድርጊቱን ክደው የተከራከሩ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ ያሉትን የሰው ምስክሮች ፣ አስረጂና ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል።

ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ስላልቻሉ ፍ/ቤቱ  የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።

በዚህም ፦
1ኛ ተከሳሽ በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ፤

ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾችን ደግሞ እያንዳንዳቸውን በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ

5ኛ ተከሳሽ በ1 ዓመት እስራትና በ1 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ቢ ሲ (ታሪክ አዱኛ) መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
129.3K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ