Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopia — TIKVAH-ETHIOPIA
ርዕሶች ከሰርጥ:
Gbe
Questionandanswer
Globalbankethiopia
Bankinethiopia
Oursharedsuccess
Furtheraheadtogether
Mpesasafaricom
Addisababa
Update
Genocide
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopia
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.34M
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2024-04-12 17:26:16
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ከፖሊስ አባላት ጋር ቶክስ በመክፈታቸው የተነገረላቸው የፋኖ መሪዎችና አባላት መገደላቸውን ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ፤
- ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣
- አቤኔዜር ጋሻው አባተ
- ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት " ፋኖ " ቡድን አባላት በከተማው " የሽበር ጥቃት ለመፈፀም እየተንቃሰቀሱ " መሆኑን የፀጥታ አካላት ባደረጉ ክትትል እንደደረሱባቸው ገልጿል።

ዛሬ " ሚሊኒየም አዳራሽ " አካባቢ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ " እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም ተኩስ መክፈታቸውን " አመልክቷል።

በዚም ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሲሞት ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል  መገደሉን ገልጿል።

አቤኔዘር ጋሻው ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በነበረው የተኩስ ልውውጥ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ቆስለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የፈኖ አባለቱ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ በመኪናቸው እንዲጭኗቸው ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበርም በማለታቸው  እንደገደሏቸው አመልክቷል።

አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethiopia
264.5K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 01:09:50
#Update #MNO

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአቶ በቴ ኡርጌሳን ግድያ በፅኑ #እንደሚያወግዝ ገለጸ።

በወንጀሉ ዙሪያ ተገቢው ምርመራ እንደሚደረግና ውጤቱ ለህዝብ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ የኦነግ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ በመቂ ከተማ #ባልታወቁ_ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን ገልጿል።

" ይህ በማንኛውም መንገድ በየትኛው አካል ይፈፀም ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ያለው የክልሉ መንግሥት ግድያውንም " በፅኑ አወግዛለሁኝ " ሲል አሳውቋል።

" ምንም እንኳን መንግሥት ከአቶ በቴ ኡርጌሳ ጋር የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረውም ከግድያው ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር የለም " ሲል ገልጿል።

ምርመራ ባልተደረገበት ሁኔታና ወንጀል ፈጻሚው ገና ባልታወቀበት ሁኔታ  ክስተቱን ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ የሚጠቀሙ ኃይሎች መኖራቸውን በማመልከት አጥብቆ አውግዟቸዋል።

" ከመንግስት ጋር የአቋም ልዩነት ስላላቸውና የፖለቲካ አቋማቸው ስለሚለይ ብቻ ግድያው በመንግሥት አካል እንደተፈፀመ ተደርጎ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፥ " የፖለቲካ ኪሳራ የደረሰባቸው የፖለቲካ ኃይሎች መንግሥትን ለግድያው ተጠያቂ በማድረግ ይህንን ሁኔታ ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው " ሲል ወቅሷል።

መንግሥት በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅም ባወጣው መግለጫ ቃል ገብቷል።

የፀጥታ ኃይሎች የግድያውን ፈፃሚ በህግ አግባብ መርምረውና አጣርተው እስካላሳወቁ ድረስ " ይህ አካል ነው ኃላፊነት የሚወስደው " ብሎ መናገር እንደማይቻል ጠቁሟል።

ማህበረሰቡ ገና ውጤቱ ሳይታወቅ እየተካሄዱ ካሉት " እከሌ ነው የገደለው " ከሚሉ ፕሮፖጋንዳዎች ራሱን መጠበቅ አለበትም ብሏል።

@tikvahethiopia
130.1K viewsedited  22:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 01:01:08
#Update

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፥ ዛሬ በባሕር ዳር ስታዲየም በነበረ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ወቅት ፥ ከቀናት በፊት በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈፀመውን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

ህዝበ ሙስሊሙ ጉዳዩን እጅግ በሰከነ መንገድ ፣ በአስተውሎት ተመልክቶ ችግሩ እንዳይባባስ ላደረገው ጥረት ምስጋና አቅርቧል።

ግድያው የዒድ አልፈጥር በዓል በሀዘን ስሜት እንዲከበር እንዳደረገውም ገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ  ፤ በአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የተፈፀመውን ግድያ " አረመኔያዊ ነው " ያለ ሲሆን " ግድያው በዓሉን #በሀዘን ውስጥ ሆነን እንድናከብረው አስገድዶናል " ብሏል።

ግድያውን " የሽብር ድርጊት ነው " ሲልም ጠርቶ " ሁሉም ሰው በአንድ ቃል ማወገዝ አለበት " ሲል ገልጿል።

ህዝበ ሙስሊሙ ከሌላው ወገኖቹ ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገባ ፣ አካባቢውን ፣ ከተማውን እንዲሁም ክልሉን የእልቂትና ውድመት ማዕከል ለማድረግ የታሰበ ግድያ ነው ሲልም አስረድቷል።

የሙስሊም ማህበረሰብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ በመመልከት የግድያው ፈጻሚዎች በህግ አግባብ ብቻ እንዲዳኙ እንጂ " እሾህን በእሾህ መንቀል " ተገቢ አይደለም በማለት ላደረገው አስተዋጽኦ ፣ መረጋጋትና ስክነት የከተማው አስተዳደር ምስጋና አቅርቧል።

ከቀናት በፊት በባህር ዳር ቀበሌ 14 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም 1 ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸው ይታወሳል።

እስካሁን ከግድያው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለ አካል ስለመኖሩ በይፋ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
127.2K viewsedited  22:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 14:36:07
#Update

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ።

ፓርቲው በግድያው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ የፓርቲው አባል እና የፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን አመልክቶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

" በነቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና በታዋቂ ሰዎች ላይ የሚደረገው ግድያ ቀጥሏል " ያለው ኦነግ የታወቂውና ተወዳጁ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሳይረሳ እና ቤተሰቦቹ እስካሁን ፍትህ ሳያገኙ የበቴን ኡርጌሳን ግድያ መስማት እጅግ አሳዛኝ ነው ብሏል።

ጃል በቴ በተወለዱበት መቂ ከተማ #በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን በመግለጫው ላይ አመልክቷል።

" ምንም እንኳን ሁኔታው ​​​​ለሁላችን እጅግ በጣም ከባድ ቢሆንም በግድያው ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረግን ነው " ሲል ገልጿል።

" ሁሉም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች እና ሰላም ወዳድ ህዝቦች አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲያደርጉ " ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
253.6K views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 13:22:42
#Update

በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ አፋጣኝ፣ ገለልተኛና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት #አፋጣኝ፣ #ገለልተኛ እና #ሙሉ_ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል " ብለዋል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉበት ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።

@tikvahethiopia
252.7K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 13:11:56
" በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም " - አቶ ጃዋር መሀመድ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምን አሉ ?

" የትኛው እጅ ነው ጨክኖ በቴ ኡርጌሳን በለሊት ከእንቅልፋቸው አስነስቶ የሚረሽነው ? እንዴትስ በቴን የሚያውቅ ሆዱ አስችሎት አይኑ እያያ  ሊገድለው ቻለ ? ወገኖች ይህ ምን ይባላል አሁን ?

በቴን ቢያንስ አውቀዋለሁ ጠንካራ የሆነ የፖለቲካ አቋም ቢኖረውም ለማንም ሆነ ለየትኛውም ቡድን ክፉ የሚያስብ ሰው አልነበረም።

እ.ኤ.አ ነሀሴ 2016 በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ተይዞ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበት ሞተ ተብሎ ለረጅም ጊዜ በሆስፒታል ውስጥ ቆይቷል።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስርና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም። ይህ ለበቴ አይገባም ነበር። " ሲሉ የአቶ በቴን ግድያ አውግዘዋል።

የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉትበት ሆቴል ተውስደው ተገድለው መንገድ ላይ ተጥለው ተገኝተዋል።

ወደ መቂ ያቀኑት የእርሻ ስራቸውን ለመመልከት እንደነበር ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የቅርብ ጓደኛቸውን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

እስካሁን ድረስ ፓርቲያቸው ኦነግ በይፋ መግለጫ አልሰጠም። በመንግስት በኩልም የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
242.9K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 12:23:02
#ዒድ_አልፈጥር

1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን ጥዋት ላይ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ተከናውኗል።

በየከተሞቹ ባሉ የዒድ ሶላት መስገጃ ስፍራዎች ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሰባሰብ የዒድ ሶላት ስነስርዓት አከናውኗል።

ከዒድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን የ1445ኛውን ዒድ አልፈጥር በዓል እያከበረ ነው።

በየከተሞቹ የነበረውን የዒድ ሶላት ስነስርዓት በፎቶ ይመልከቱ @tikvahethmagazine

በድጋሜ መልካም በዓል !

ፎቶ፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው (አዲስ አበባ)

@tikvahethiopia
238.1K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 22:32:22
#የፀሀይ_ግርዶሽ

ዛሬ ሰኞ በተለያዩ ሀገራት ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽ እየታየ ይገኛል።

በተለይ በሜክሲኮ እና አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ እየታየ ነው።

የተለያዩ ቦታዎች በፀሀይ ግርዶሹ ምክንያት ከ3 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በሙሉ #ጨለማ_ተውጠው ታይተዋል።

ክስተቱንም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ነው።

የፀሀይ ግርዶሽ #ጨረቃ በምድር እና በፀሀይ  መካከል ስታልፍ የፀሀይን እይታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በምትጋርድበት ጊዜ የሚከሰት ነው። 

@tikvahethiopia
93.7K views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 22:01:39
#Update

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምን አለ ?

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዛሬ ማምሻውን ይፋዊ መግለጫ ሰጠ።

በዚህም መግለጫው ባለፉት #8_ወራት በአማራ ክልል በመንግስትና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ህዝቡን እጅግ የከፋ ዋጋ እያስከፈለዉ መሆኑን ገልጿል።

" በዋናነት በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ፣ መፈናቀል፣ ዘረፋ፣ መታገትና መገደል ከጊዜ ጊዜ #እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነው " ብሏል።

" ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ጉዳዩ ከቀን ወደ ቀን ንጹሀን ዜጎችን በማገትና በመሰወር እንዲሁም በመግደል የክልሉን ህዝብ በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል " ሲል ምክር ቤቱ አስረድቷል።

እንደማሳያም ፦

በቀን በ29/7/16 በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 የመቅሪብ ሶላት ሰግደዉ ወደ ቤታቸዉ በሚሄዱ አማኞች ላይ ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች 4 የአንድ ቤተሰብ አባላትን እና 1 ጎረቤታቸዉን በመግደል ተሰዉረዋል፡፡

በ28/07/16 በጎንደር ከተማ ማክሰኝት አካባቢ 4 ሙስሊሞች ተገድለዋል፡፡

29/07/16 በሞጣ ከተማ አንድን ወጣት ካገቱ በኋላ ቤተሰቦቹን በማስፈራራት 300 ሺህ ንር ተቀብለዉ ታጋቹን በአሰቃቂ ሁኔታ #ገድለዉ ጥለዉታል፡፡

በቢቸና ከተማ በቀን 26/07/16 ንጹሀን ባልና ሚስት " ለምን ለመንግስት ግብር ከፈላችሁ " ተብለዉ በግፍ ተገድለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በአጠቃላይ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ባለፉት 8 ወራት ፦
- ከ80 በላይ ሙስሊሞች መገደላቸውን
- በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መፈናቀላቸውን
- አርባ ሰባት (47) ሰዎች መታገታቸውን
- ከ260 በላይ ዘረፋዎች መፈፀማቸውን አሳውቋል።

" ይህን ዘረፋ፣ ብዙ ስቃይ እና እንግልት፤ መገደልና መፈናቀል በጽኑ እናወግዛለን " ብሏል።

" ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም መንግስት ፣ ሰላማዊዉ የክልሉ ህዝብ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች ፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን እንዲወጡ  " ሲል ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
120.1K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 18:23:14
የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ነው።

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ አልታየችም ፤ በመሆኑም የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።

ነገ ማክሰኞ የረመዷን #የመጨረሻው ሰላሳኛ ቀን ይሆናል።

@tikvahethiopia
279.7K viewsedited  15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ