Get Mystery Box with random crypto!

' በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም ' - አቶ ጃዋር | TIKVAH-ETHIOPIA

" በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም " - አቶ ጃዋር መሀመድ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምን አሉ ?

" የትኛው እጅ ነው ጨክኖ በቴ ኡርጌሳን በለሊት ከእንቅልፋቸው አስነስቶ የሚረሽነው ? እንዴትስ በቴን የሚያውቅ ሆዱ አስችሎት አይኑ እያያ  ሊገድለው ቻለ ? ወገኖች ይህ ምን ይባላል አሁን ?

በቴን ቢያንስ አውቀዋለሁ ጠንካራ የሆነ የፖለቲካ አቋም ቢኖረውም ለማንም ሆነ ለየትኛውም ቡድን ክፉ የሚያስብ ሰው አልነበረም።

እ.ኤ.አ ነሀሴ 2016 በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ተይዞ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበት ሞተ ተብሎ ለረጅም ጊዜ በሆስፒታል ውስጥ ቆይቷል።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስርና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም። ይህ ለበቴ አይገባም ነበር። " ሲሉ የአቶ በቴን ግድያ አውግዘዋል።

የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉትበት ሆቴል ተውስደው ተገድለው መንገድ ላይ ተጥለው ተገኝተዋል።

ወደ መቂ ያቀኑት የእርሻ ስራቸውን ለመመልከት እንደነበር ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የቅርብ ጓደኛቸውን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

እስካሁን ድረስ ፓርቲያቸው ኦነግ በይፋ መግለጫ አልሰጠም። በመንግስት በኩልም የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia