Get Mystery Box with random crypto!

#ዒድ_አልፈጥር 1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታ | TIKVAH-ETHIOPIA

#ዒድ_አልፈጥር

1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን ጥዋት ላይ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ተከናውኗል።

በየከተሞቹ ባሉ የዒድ ሶላት መስገጃ ስፍራዎች ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሰባሰብ የዒድ ሶላት ስነስርዓት አከናውኗል።

ከዒድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን የ1445ኛውን ዒድ አልፈጥር በዓል እያከበረ ነው።

በየከተሞቹ የነበረውን የዒድ ሶላት ስነስርዓት በፎቶ ይመልከቱ @tikvahethmagazine

በድጋሜ መልካም በዓል !

ፎቶ፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው (አዲስ አበባ)

@tikvahethiopia